በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በሶማልያ ከፍተኛ ድርቅ ሊኖር እንደሚችል አስጠነቀቀ


በሶማልያ የአየር ለውጥ በድርቅና በጎርፍ የተጎዱ ነዋሪዎች መጠለያ
በሶማልያ የአየር ለውጥ በድርቅና በጎርፍ የተጎዱ ነዋሪዎች መጠለያ

በሶማልያ ስድስት የአገሪቱ አካባቢዎች ከሚያዝያ እስከ መጭው ሰኔ ድረስ ዝናብ ካልጣለ ከፍተኛ ረሀብ ሊያስከትል የሚችል ድርቅ ሊከሰት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ትናንት በሰጡት መግለጫ አስጠንቅቀዋል፡፡

ቃል አቀባዩ እስከ መጋቢት 29/2014 ድረስ 5.5 ሚሊዮን ወንዶች፣ ሴቶችና ህጻናት ተረጅዎችን ለመርዳት ከተጠየቀው የ1.5 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ የተገኘው 4.4 ከመቶው እጅ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአገር ውስጥ የተፈናቀሉትን 719ሺ ሰዎች ጨምሮ 4.9 ሚሊዮን ሶማልያ ዜጎች በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ መግለጫ አመልክቷል፡፡

ቃል አቀባዩ እንደተገመተው የምግብ ዋጋ እየጨመረ ከሄደና ተጎጂ ለሆኑ ወገኖችም የሰብአዊ እርዳታ ካልጨመረ ከፍተኛ ችግር ሊያስከትል ይችላል ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG