በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬንና አጋሮችዋ የባቡር ጣቢያውን ጥቃትና ሩሲያን አወገዙ


የዩክሬን ወታደሮች በክራማቶርስክ ባቡር ጣቢያው አቅራቢያ በሩሲያው ጥቃት በወደሙ ተሽከርካሪዎች አጠገብ ዩክሬን እኤአ ሚያዝያ 8 2022
የዩክሬን ወታደሮች በክራማቶርስክ ባቡር ጣቢያው አቅራቢያ በሩሲያው ጥቃት በወደሙ ተሽከርካሪዎች አጠገብ ዩክሬን እኤአ ሚያዝያ 8 2022

ዩክሬንና አጋሮችዋ ትናንት ዓርብ በባቡር ጣቢያው የደረሰውን ጥቃት ያወገዙ ሲሆን ለጥቃቱ ሩሲያን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

ጦርነቱን የሚሸሹ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች በተሰባሰቡበት ዩክሬን ውስጥ በሚገኝ አንድ ባቡር ጣቢያ ላይ በደረሰው የሩሲያ የሚሳዬል ጥቃት

የባቡር ጣቢያው ኃላፊዎች ቢያንስ 52 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡

ጥቃቱ ከተነገረ አንድ ቀን በኋላም ዛሬ ቅዳሜ የሰዎች መፈናቀሉ መቀጠሉ ተነግሯል፡፡

“ሆን ተብሎ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው” ያሉት የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ፣ ለትናንቱ ጥቃት ዓለም ጠናካራ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ “ትናንት የታየው በሩሲያ ኃይሎች የተፈጸመና በጦር ወንጀልነት የሚወሰድ ሌላው የቅርብ ጊዜ ጥቃት ነው” ብለዋል፡፡

አገራቸው ራሷን እንድትከላከል የምዕራባውያን ደጋፊዎች ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩም ፕሬዚዳንቱ ተማጽነዋል፡፡

ዘለንስኪ ቅዳሜ ምሽቱን ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት “ የመላው ዓለም ትኩረት መሆን ያለበት በያንዳንዷ ደቂቃ ያለቸውን መመዝገብ ነው፣ ይህን ያደረገው ማነው? ያን ትዕዛዝ የሰጠው ማነው? ሚሳዬሉ የመጣው ከወዴት ነው? ያጓጓዘውስ ማነው? ትዕዛዙን የሰጠው ማነው? ለጥቃቱስ ከስምምነትስ የተደረሰው እንዴት ነው?” የሚሉት መጠየቅ አለባቸው ብለዋል፡፡

ሩሲያ ድርጊቱን አስተባብላለች፡፡ “የዩክሬን ሠራዊት ወደ ባቡር ጣቢያው በመተኮስ በስፍራው ለሞቱት ሰላማዊ ሰዎች ሞስኮን ተጠያቂ ለማድረግ የታቀደ ተግባር ነው” ስትልም ከሳለች፡፡

የሩሲያው መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ የዩክሬንን ጦር አቀማመጥና የሚሳዬሎቹን አቅጣጫ ዝርዝር በመግለጽ ሁኔታውን ለማብራራት ሞክረዋል፡፡

ምዕራባውያንና የዩክሬን ባለሙያዎች ግን ሚሳዬሎቹን የተኮሱት ሩሲያውን ናቸው ይላሉ፡፡

የእንግሊዝ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ በሰጡው መግለጫ “ሩሲያ በትናንቱ የባቡር ጣቢያው የሮኬት ጥቃቷ እንዳሳየችው፣ ውጊያ ውስጥ ያልተሳተፉ ሰላማዊ ዜጎችን ማጥቃቷን ቀጥላለች” ብሏል፡፡

ዘለንስኪ ነገ በአሜሪካው የሲቢኤስ ቴሌቭዥን 60 ሚኒት ፕሮግራም ላይ ይተላለፋል በተባለው ቃለ መጠይቃቸው፣ ኢላማ የተደረጉ ሰላማዊ ሰዎች ከሚገኙበት ተቋማት ካርታ ጋር ፣ በዩክሬን ጦር የተያዘ አንድ የሩሲያ አብራሪ (ፓይለት) መኖሩንም ተናግረዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ባስተላለፉት የትዊት መልዕክት ጥቃቱን “በሩሲያ የተፈጸመ ዘግናኝ ግፍ” ብለውታውል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክም የዋና ጸሀፊውን የአንቶኒዮ ጎትሬዥ ቃል በመድገም “ይህን ጨካኝ ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG