በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለዩክሬናውያን ተፈናቃዮች ተጨማሪ ዕርዳታ ያስፈልጋል ተባለ


ለዩክሬናውያን ተፈናቃዮች ተጨማሪ ዕርዳታ ያስፈልጋል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:59 0:00

ለዩክሬናውያን ተፈናቃዮች ተጨማሪ ዕርዳታ ያስፈልጋል ተባለ

በሃገራቸው እየተካሄደ ካለው ውጊያ እና የሩሲያ ጦር ከሚፈጽመው እየጨመረ የመጣ የጭካኔ ጥቃት በመሸሽ ቀያቸውን ጥለው በመኮብለል ላይ ያሉ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ዩክሬናውያንን ለመርዳት የሰብዓዊ ረድኤት አቅሙን በማጠናከር ላይ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ።

ባለፈው የካቲት 17/2014 ዓ.ም የተጀመረው የሩሲያ የዩክሬን ወረራ ሚሊዮኖችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቀያቸው በማፈናቀል ከዚህ ቀደም ከታዩት የሰብዓዊ ቀውሶች አንዱ የሆነውን ለመቀስቀሰ ምክኒያት ሆኗል። በሲቪል ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ እና መጠነ ሰፊ ሥፍራዎችን ያካለሉ በዩክሬን ከተሞች ላይ የተፈጸሙ የቦምብ ድብደባዎች ቁጥራቸው 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን የሚደርሱ ዩክሬውያን ቀያቸውን ጥለው ወደ ጎረቤት አገሮች እንዲኮበልሉ ምክኒያት መሆኑን የዓለሙ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ዩኤንኤችሲአር አመልክቷል። ተጨማሪ 7 ነጥብ 1 ሚልዮን ዩክሬናውያን የአገር ውስጥ ተፈናቃይ ለመሆን መገደዳቸውም ተዘግቧል።

ድርጅቱ አክሎም በፍጥነት እየጨመረ የመጣውን ተፈናቃይ ፍላጎት ለማሟላት አገራቸውን ጥለው የኮበለሉትንም ሆነ እዚያ ዩክሬን ውስጥ ተፈናቅለው የሚገኙትን ሰዎች ለመርዳት የሚያደርገውን ጥረት ማሳደጉን አመልክቷል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ማቲው ሳልትማርሽ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያዎች ብዙዎችን መርዳት በሚችሉበት ደረጃ እንዲስፋፉ እየተደረገ መሆኑን አመልክተው፤ የእርዳታ አቅርቦቱን ትኩስ ውጊያ እየተካሄደባቸው ካሉ አካባቢዎች መድረስ ግን አዳጋች መሆኑን ይናገራሉ።

አያይዘውም “ሆኖም የረድኤት ሠራተኞች በውጊያ ከተጠመዱት እንደ ማሪዮፑል እና ኸርሰንን ከመሳሰሉት አካባቢዎች ለመድረስ መሥራታቸውን ግን አላቆሙም” ብለዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ለሳምንታት ሳያቋርጥ የወረደባቸውን የአየር ድብደባ፤ እንዲሁም የውሃ፣ የነዳጅ እና የኤሌክትሪክ አቅርቦት እጥረት ተቋቁመው ነው ከዚህ መድረሳቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። “በሌላ በኩል ቡድናችን በጸሃይ ኃይል የሚሰሩ አምፖሎችን፣ ብርድ ልብስ፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ የሕጻናት ምግብ እና ውሃ የማያስገቡ ለመጠለያ መሥሪያነት የሚያገለግሉ ሸራዎችን ማድረስ ችሏል።” ብለዋል።

አብዛኛው ዩክሬውያን ወደ ጎረቤት ፖላንድ በመፍለስ ላይ መሆናቸውን የተናገሩት ሳልትማርሽ ፖላንድ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ ወደዚያች አገር የመጡ ቁጥራቸው ከ2 ነጥብ አምስት ሚልዮን በላይ ተፈናቃዮች ተቀብላ ማስተናገዷን ገልጠዋል።

ድርጅታቸው ቀደም ሲል ተፈናቃዮቹን ለመርዳት የወሰደው የመጀመሪያ ምላሽ በዩክሬይን ባለው እርሳቸው “እጅግ ዘግኛኝ” ባሉት ሁኔታ ሳቢያ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን አመልክተዋል። ሳልትማርሽ እንደ እውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ ጠይቆት የነበረው የ550 ነጥብ 6 ሚልዮን ዶላር አሁን ቀውሱ ለሚጠይቀው ወጭ በቂ አይደለም።

በመሆኑም የተሟላ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አዲስ በጀት በያዝነው ወር መጀመሪያ ይፋ ያደርጋል።

XS
SM
MD
LG