በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቡነ ፍራንሲስ የዩክሬኑን እልቂት አወገዙ

የሮማው ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ “የቡቻው እልቂት” ብለው የጠሩትን የዩክሬኑን የሩሲያ ድርጊት አወገዙ፡፡

አቡኑ ውግዝታቸውን ያሰሙት ዓለም አቀፍ ቁጣን መቀስቀሱ የተነገረለትና ከቀናት በፊት በዩክሬን ጎዳናዎች ላይ የታዩትን አስክሬኖችና የጅምላ መቃብሮች አስመልክቶ ነው፡፡

በቫቲካን በየሳምንቱ ለአድማጮቻቸው በሚያሰሙት ንግግር ዛሬ እንደተናገሩት ከዩክሬን የሚመጣው ዜና ከእፎይታና መልካም ዜና ይልቅ “አዳዲስ ግፎችን አምጥቷል” ብለዋል፡፡

ጳጳሱ በንግግራቸው “ይህን ጦርነት አቁሙ! መሳሪያዎች ዝም ይበሉ፡፡ ሞትና ውድመት መዝራት ተው” ብለዋል፡፡

አቡኑ ከቡቻ የመጣነው የተባለውን ሰንደቅ መያዛቸውም ተነግሯል፡፡

ሩሲያ ምንም ዓይነት የጦር ወንጀል አለመፈጸሟን ገልጻ፣ ዩክሬንን ትይዕንቶችን ትፈብርካለች ስትል ከሳለች፡፡


XS
SM
MD
LG