በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባቡል ኸይር - ለብዙዎች የመኖር ተስፋን የፈነጠቀ የበጎ አድራጎት ድርጅት


ባቡል ኸይር - ለብዙዎች የመኖር ተስፋን የፈነጠቀ የበጎ አድራጎት ድርጅት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:40 0:00

ባቡል ኸይር - ለብዙዎች የመኖር ተስፋን የፈነጠቀ የበጎ አድራጎት ድርጅት

በበርካታ ማኅበራዊ ቀውሶች በመፈተን ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ፣ የአቅማቸውን ለማበርከት ከሚታትሩ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አንዱ ነው፤ ‘የበጎ ሥራ በር’ የሚል ትርጓሜ ያለው - ባቡል ኸይር፡፡

ከሁለት ዓመታት በፊት በ2012 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ በ16 በጎ ፈቃደኛ ሴቶች የተቋቋመው ባቡል ኸይር፣ አሁን ላይ ከ2800 በላይ አቅመ ደካሞችን በየቀኑ ይመግባል፡፡ ጓደኞቿን እና ቤተሰቧን አስተባብራ ድርጅቱን የመሰረተችው ወ/ሮ ሀናን ማህሙድ “ሁለት ታዳጊ ሴቶች በትምሕርታቸው ሰዓት “ምግብ ፍለጋ ሲንከራተቱ” ማየቷ ለሐሳቡ መነሻ እንደሆናት ትናገራለች።

ይህ በዐይኗ ያየችው እና የብዙ ኢትዮጵያውያን መገለጫ የሆነው አጋጣሚ ልቧን በመንካቱ፣ ምስኪኖች ምንም መስፈርት ሳያስፈልጋቸው የሚመገቡበትን የበጎ አድራጎት ማዕከል ለመክፈት በፍጥነት እንቅስቃሴ ጀመረች፡፡ ከዚያም ከጓደኞቿ ጋር በመነጋገር ያላቸውን ገንዘብ በማዋጣት እንዲሁም ጌጣጌጦቻቸውን ጭምር በመሸጥ “ባቡል ኸይር” የተሰኘውን እና ዛሬ የብዙ አቅመ ደካሞች መጠጊያ የሆነውን የበጎ አድራጎት ድርጅት ከፈቱ፡፡

የክርስትናም ይሁን የእስልምና እምነት ተከታዮች እንደየ እምነታቸው የሚስተናገዱበት ድርጅቱ አሁን ላይ አቅመ ደካሞችን በተለያዩ ሙያዎች እያሰለጠነ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ከማድረግ ባለፈ፣ የደም ልገሳ፣ የምስኪኖችን ቤት የማደስ፣ የማማከር እና መሰል አገልግሎቶችንም ይሰጣል፡፡

57 ተቀጣሪ ሠራተኞች ባሉት በዚህ የበጎ አድራጎት ድርጅት ብዙዎች በበጎ ፈቃድም ያገለግላሉ፡፡ ምንም እንኳን ድርጅቱ አሁን ላይ የተለያዩ ግለሰቦች እንደአቅማቸው በሚያደርጉለት ድጋፍ እና በመስራቾቹ ጥረት የቀጠለ ቢሆንም፣ ካለው ፍላጎት አንጻር ግን ብዙ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የድርጅቱ መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀናን ማህሙድ ገልጻለች፡፡

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ባለሥልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች ድርጅቱን በተለያዩ ጊዜያት ቢጎበኙም ያደረጉለት ድጋፍ ግን የለም የምትለው” ወ/ሮ ሀናን፣ በየዕለቱ ከሚያጋጥሟ ክስተቶች የታዘበችውን ስትገልጽ፣ በኢትዮጵያ ያለው ማኅበራዊ ቀውስ እንደሚያሰጋት ታነሳለች፡፡ በመሆኑም አቅም ያለው ሁሉ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪዋን አቅርባለች፡፡

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG