በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የ100 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ እንደምትሰጥ ዛሬ አስታወቀች


ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የ100 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ እንደምትሰጥ ዛሬ አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:56 0:00

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የ100 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ እንደምትሰጥ ዛሬ አስታወቀች

ለዩክሬን የ100 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ እንደምትሰጥ ዛሬ ያስታወቀችው ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ጥላለች። አንተኒ ብሊንክን በኔቶ አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ለመገኘት ብራስልስ ገብተዋል።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው የብራስልሱ የኔቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስሮች ስብሰባ በዩክሬኑ ግጭት ላይ የሚመክር መሆኑም ተነግሯል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስርት አንተኒ ብሊንከን ብራስልስ ከመድረሳቸው በፊት ትናንት ምሽት ባወጡት መግለጫ “የሩሲያ ኃይሎች በቡቻና በመላ ዩክሬን የፈጸሙት ዘግኛኝ ጥቃት ዓለምን ያስደነገጠ ነው” ብለዋል።

ብሊንክ አያይዘውም “ዩናይትድ ስቴትስና አጋሮቿ የዩክሬን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት እንዲጠበቅ ድጋፋቸውን በመስጠት ከጎናቸው በፅናት ይቆማሉ” ብለዋል።

በሌላ በኩል ዩናይትድ ስቴትስ ዩክሬን የሩሲያን ጥቃት ለመከላከል የሚያስፈልጋትና እስካሁንም ውጤታማ በሆነ መንገድ ሲከላከሉበት የቆዩትን ተጨማሪ የጦር መከላከያ መሳሪያዎችን በመስጠት እንደምትቀጥል የመከላከያ ሚኒስቴሯ ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ ተናግረዋል።

የኔቶ ዋና ፀሀፊ የንስ ሽቶልተንበርግም የኔቶ አባላት ለዩክሬን ተጨማሪ ድጋፍ ለመስጠት ቁርጠኞች መሆናቸውን፣ ከኢንተርኔትና የኮምፕዩተር ሥርዓት ደኅንነት ድጋፍ ሌላ ሰብአዊና የገንዘብ እርዳታም እንደሚሰጡ ዋና ፀሀፊው ጨምረው ገልጸዋል። አያይዘውም “ለሩሲያ ወረራና ጣልቃ ገብነት ተጋላጭ ሊሆኑ ለሚችሉ ጆርጂያና ቦስኒያ ሄርዘጎቪናን ለመሳሰሉ ሌሎቹ የኔቶ አባል አገሮችም ተጨማሪ እርዳታ ለማድረግ ሊወሰን እንደሚችል አመልክተዋል።

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድሚትሮ ኩሌባ ለኔቶው የሚኒስትሮች ስብሰባ ነገ፤ ሀሙስ ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG