በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አልሸባብ የሶማሊያ መሪዎችን ለመግደል ማቀዱን የሶማሊያ ደህንነት አስታወቀ


የፖሊስ መኮንኖች በሥራ ላይ በሞቃዲሾ ሶማሊያ እአአ ሚያዚያ 23/2022
የፖሊስ መኮንኖች በሥራ ላይ በሞቃዲሾ ሶማሊያ እአአ ሚያዚያ 23/2022

የሶማሊያ ደህንነት ተቋም አልሸባብ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብደላ መሀመድና እና ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌን ለመግደል አቅዷል ሲል ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የአገሪቱ ብሄራዊ የደህንነትና ጸጥታ ተቋም ትናንት ባወጣው የትዊት መልዕክት የግድያውን ሴራ በበላይነት የሚያቀነባብረው መሀመድ ማሂር መሆኑን ገልጿል፡፡

“ተቋሙ ስለእቅዱ ዝርዝር መግለጫ ያልሰጠ ሲሆን፣ለባለሥልጣናቱግን መረጃውን መስጠቱን አስታውቋል”ሲል የቪኦኤ የሶማሊኛ ክፍል ዘጋቢ መሀመድ ሼክ ኑር ከሞቃድሾ የላከው ዘገባ አመልክቷል፡፡ የግድያው እቅድ የመጣው ሶማልያ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን ብሄራዊ ምርጫ ለማካሄድ በምትገኝበት ወቅት ነው፡፡

ይህንኑ ሂደት ለማደናቀፍ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው አልሸባብ በቅርቡ ተከታታይ ጥቃቶችን ሲያካሂድ መቆየቱ በዘገባው ተመልክቷል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ አልሸባብ ኃላፊነቱን የወሰደበት፣ እኤእ መጋቢት 23 በሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ የተካሄደውና 6 ሰዎች የሞቱበት ጥቃት ይገኝበታል፡፡

XS
SM
MD
LG