በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በኢትዮጵያ ንግድና ምጣኔ ሐብት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ ተገለፀ


የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በኢትዮጵያ ንግድና ምጣኔ ሐብት ላይ ተፅኖ ማሳደሩ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:01 0:00

የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በኢትዮጵያ ንግድና ምጣኔ ሐብት ላይ ተፅኖ ማሳደሩ ተገለፀ

የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ ጎጂ ተፅኖ ማሳደሩን የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አስታወቀ።

ኢትዮጵያ ከሩሲያና ከዩክሬን ብረትና ስንዴ ስታስገባ፤ ቡናና ሻይ ቅጠል ደግሞ ስትልክ መቆየቷን የገለፁት የምክር ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደበበ አበበ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍም በትብብር ለመሥራት ከሁለቱም ሃገሮች ጋር የተለያየ ሥምምነት እንደነበራት ተናግረዋል።

እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በ2020 ዓ.ም ኢትዮጵያ ከሩሲያ 44. 2 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ስንዴና ብረት ማስገባቷንና በአንፃሩ ደግሞ 11.4 ሚሊዮን ዶላር ቡናና ሻይ ቅጠል መላኳን አቶ ደበበ ተናግረዋል።

ከዩክሬንም እንዲሁ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በ2018 ዓ.ም 157 ሚሊዮን ዶላር ስንዴና ብረት በ2020 ደግሞ ኢትዮጵያ የ 1.1 ሚሊዮን ዶላር የንግድ እቃዎች ወደ ዩክሬን መላኳን አቶ ደበበ ተናግረዋል። ስለዚህ የምርቶቹ መቋረጥ በብረት ላይ ከፍተኛ የዋጋ መጨመር መታየቱን ገልፀዋል።

በሌላ በኩልም ሩሲያ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኦፕሬሽን የሚል መድረክ ከጦርነቱ ቀደም ብሎ መከፈቱን የገለፁት አቶ ደበበ ከዩክሬን ጋር ደግሞ በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሞ እንደነበር ገልፀዋል።

በመሆኑም በጦርነቱ ምክኒያት ከኢንቨስትመንትና ከንግድ ትስስር አንፃር ከፍተኛ ጉዳት እንደሚኖረው አቶ ደበበ ተናግረዋል። በተጨማሪም ሁለቱ ሃገሮች የአውሮፓና የእስያ መተላለፊያ በመሆናቸው ምክኒያት በተከሰተው የባሕር ትራንስፖርት ተፅኖ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ ጭማሪ መታየቱን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መርከቦች አገልግሎት ወጪ የ42 በመቶ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱንም ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG