በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ቁጥር የሚወሰነው በማን ነው?


ፎቶ ፋይል፦ የእርዳታ ጭኖ ወደ ትግራይ የሚጓዝ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪ
ፎቶ ፋይል፦ የእርዳታ ጭኖ ወደ ትግራይ የሚጓዝ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪ

የትግራይ ክልል ሕዝብን አስቸኳይ የምግብ ፍላጎት ለማሟላት በየቀኑ 300 የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንደሚገባቸው የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አትንኩት ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁ ሲሆን ወደ ትግራይ ክልል የሚገቡ የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ቁጥር የሚወሰነው በለጋሾች አቅም መሆኑን ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ ወደ ክልሉ በሚገቡ የጭነት ተሸከርካሪዎች መጠን ላይ የተቀመጠ ገደብ እንደሌለ ተናግረዋል።

መንግስት ለትግራይ ክልል የእርዳታ ምግብ ገዝቶ የማቅረብ ሚና ሊወጣ ይገባል በሚል የክልሉ ባለሥልጣን ላቀረቡት ክስ በሰጡት ምላሽ ደግሞ፤ መንግሥት በሌሎችም ክልሎች ያለውን ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ አቅም በፈቀደ ድጋፍ ማቅረብ ይቀጥላል ብለዋል ሚኒስትሩ።

እርዳታው በአግባቡ እንዲደርስ የህወሓት ወገን ግጭት ማቆም አለበት ያሉት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ፣ ይሁንና ህወሓት የገባውን ቃል በመተግበር ላይ አይደለም ብለዋል።

የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል ከገቡ ከ109 ቀናት በኋላ 21 ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መግባታቸውን የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ መግለፃቸው ይታወሳል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ቁጥር የሚወሰነው በማን ነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:53 0:00

XS
SM
MD
LG