በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድሬ ሮቃ ጃራ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ


ድሬ ሮቃ ጃራ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:56 0:00

ድሬ ሮቃ ጃራ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ

ከሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ ወደ ሃብሩ ወረዳ ድሬ ሮቃ ጃራ መጠለያ ጣቢያ የተዘዋወሩ ተፈናቃዮች መሰረታዊ የምግብና የመጠለያ አቅርቦት እንደማያገኙ አስታወቁ፡፡

ተፈናቃዮቹ የምግብና የሌሎች ድጋፎች አቅርቦት አነስተኛ ከመሆኑ ባሻገር የሚከፋፈለውም “በዘመድና በቤተሰብ ቅርበት ነው” ሲሉ ይከሳሉ፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መካከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት የተፈናቃዮቹን ክስ “መሰረት የለሽ” ሲል አጣጥሎታል፡፡

የምግብና የመጠለያ እጥረቱ የተከሰተው ቃል የገቡ አካላት ማቅረብ በሚገባቸው ልክና መጠን ባለማቅረባቸው እንደሆነ ተጠሪ ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባባሪያ ኮሚሽን በበኩሉ ከመንግሥት ውጭ በተለይ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ተፈናቃዮችን መልሶ በማቋቋም በኩል የሚያደርጉት ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

XS
SM
MD
LG