በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እርዳታ የጫኑት መኪኖች ትግራይ መድረሳቸውን ክልሉ አስታወቀ


እርዳታ የጫኑት መኪኖች ትግራይ መድረሳቸውን ክልሉ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00

እርዳታ የጫኑት መኪኖች ትግራይ መድረሳቸውን ክልሉ አስታወቀ

የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል ከገቡ ከ109 ቀናት በኋላ 21 ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መግባታቸውን የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ገለፀ።

አሁን ያለውን የክልሉን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ፍላጎት ለማሟላት በየቀኑ 300 የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንደሚገባቸው የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ በሠጧቸዉ መግለጫዎች፤ የእርዳታ አቅርቦቱ ወደ ትግራይ ክልል መግባት እንዲችል የህወሓት ታጣቂዎች ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች ለቀው መውጣት እንዳለባቸው ሲገልፁ መቆየታቸው ይታወሳል።

በየቀኑ ወደ ትግራይየሚገቡ የዕርዳታ መኪናዎች ቁጥር እንዴትና በማን እንደሚወሰን ግን በመንግሥትም ሆነ ከለጋሽ ድረጅቶች ወገን የተገለጸ ነገር የለም።

XS
SM
MD
LG