በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሃርጌሳ የእሳት አደጋ በሰዎችና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ


በሃርጌሳ፣ ዋሄን ገበያ ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ እአአ ሚያዚያ 2/2022
በሃርጌሳ፣ ዋሄን ገበያ ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ እአአ ሚያዚያ 2/2022

ባለፈው ቅዳሜ በሰሜን ሶማሊያ ሀርጌሳ ዋና ከተማ ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ 28 ሰዎች መቁሰላቸውና በርካታ የንግድ ድርጅቶች መውደማቸውን የከተማ ባለሥልጣኖችና የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

እንደ ዓይን እማኞች ገለጻ ሌሊቱን የተነሳው የእሳት አደጋ ከአሮጌዎቹ የከተሞቹ አካባቢ ከነበረው የገበያ ስፍራ በመነሳት ወደሌሎቹ አካባቢዎች መዛመቱ ተገልጿል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው የእሳት አደጋ ምስል በአካባቢው የነበሩ የገበያ መደብሮች በሙሉ በትልቅ ነበልባልና ጭስ ታፍነው እንደነበር ያሳያል፡፡

አደጋው በደረሰበት ወቅት አካባቢውን የጎበኙት የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሲ ቢሂ በአደጋው ከቆሰሉት 28 ሰዎች ውስጥ 9ኙ ሴቶች መሆናቸውን ገልጸው በአደጋው የሞተ ሰው አለመኖሩን አስታውቀዋል፡፡

የአደጋው ምክን ያት ባይታወቅም የአካባቢው ነጋዴዎች ግን ከኤሌክትሪክ አደጋ ጋር የተያያዘ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ሶማሊላንድ ከሶማልያ እኤአ በ1991 ከሶማልያ ተገንጥላ የራሷን መንግሥት የመሰረተች መሆኗ ይታወቃል፡፡

ባላፈው ወር የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ቢሂ አብዲ ዋሽንግተንን የጎበኙ ሲሆን ለሶማሌ ላንድ እውቅና እንዲሰጣት ያቀረቡት ጥያቄ ውጤት ባያስገኝላቸውም በውጤቱ የተደሰቱ መሆኑን ከአሜሪካ ድምፅ የሱማልኛ ክፍል ጋር በነበራቸው ቆየታ ተናግረዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትም ሆነ የባይደን አስተዳደር አንድነቷ ለተጠበቀ ሶማልያ ያላቸውን ቁርጠኝነት በመግለጽ ይሁን እንጂ ከሶማሌላንድ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት የጠነከረ እንዲሆን የሚፈልጉ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG