በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓክሲታን ጠ/ፍርድ ቤት የታገደውን የጠ/ሚኒስትሩን የመተማመኛ ድምፅ አግባብነት ይመለከታል


በኢስላማባድ የፓኪስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት
በኢስላማባድ የፓኪስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የፓክሲታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካሃን የአገሪቱ ምክር ቤት የመተማመኛ ድምፅ እንዳይሰጥባቸው ምክር ቤቱን ለማገድ የወጣው ውሳኔ ህገ መንግሥታዊ አይደለም ሲሉ የምክር ቤት አባላት ያቀረቡትን ተቃውሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መመልከት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

342 አባላት ያሉት የአገሪቱ ምክር ቤት ውስጥ ያሉት ተቃውሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ካህንን ፓኪስታንን የሚመሩበት መንገድ የተዛባ ነው በማለት ከሥልጣን እንዲነሱ ትናንት እሁድ የመተማመኛ ድምጽ ለመስጠት ዝግጅት እንደነበራቸው ተመልክቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከሥልጣን ለማንሳት የዩናይትድ ስቴትስ እጅ አለበት የሚለውን ክስ ተቃዋሚዎቹ የምክር ቤት አባላት አልተቀበሉትም፡፡

ይሁን እንጂ ባልተጠበቀ ሁኔታ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ሊተላለፍ የነበረውን የመተማመኛ ድምፅ እንዳይሰጥ ያገዱት የምክር ቤቱ ተጠባባቂ አፈጉባኤ ቃሲም ሻ ሱሪ “ማንም የውጭ ሃይል በህዝብ የተመረጠን መንገስት በሴራ ሊጥለው አይችልም፡፡” ብለዋል፡፡

“ስለሆነም የመተማመኛው ድምፅ የአገሪቱን ሉዓላዊ አንድነት የሚጋፋ ስለሆነ ውሳኔው ተግባራዊ እንዲሆን አልፈቅድም” ሲሉ ውሳኔውን ያገዱት መሆኑን ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል፡፡

ዋሽንግተን በተደጋጋሚ የተሰነዘረባትን ክስ እውነትነት የለውም ስትል አስተባብላለች፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ትናንት እሁድ ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ የፓኪስታንን ህገመንግስታዊ ሂደትና ህግ እናከብራለን እንደግፋለን” ብለዋል፡፡

አፈ ጉባኤው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የቀረበውን የመተማመኛ ድምፅ ውድቅ ካደረጉ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክር የፓኪስታን ፕሬዚዳንት አሪፍ አልቪ ትናንት እሁድ ባስተላለፉት ውሳኔ ህግ መንግሥቱን በመጥቀስ ምክር ቤቱ እንዲበተን አዘዋል፡፡

በ90 ቀናት ውስጥ ሌላ ምርጫ እንዲካሄድም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካሃንም እንዲሁ ካቢኒያቸውን በትነዋል፡፡ እየተወሰዱ ያሉት ውሳኔዎች ኒዩክለር የታጠቀችውን የደቡብ እስያ አገር ፓክሲስታንን ከፖለቲካ ቀውስ ውስጥ የከተታት መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ሁሉም ዓይኖች በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን እስከ ነገ ማክሰኞ ድረስ ፍርድ ቤቱ የማይሰበሰብ መሆኑን ተነግሯል፡፡ ተችዎች ከተፈጠረች 74 ዓመት በሞላት ፓኪስታን የሠራዊቱ ተጽእኖ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

የፓክሲታን መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል ባርባር ኢፍቲካር ትናንት እሁድ ለቪኦኤ እንደተናገሩ አገሪቱ ውስጥ ለተፈጠረው ቀውስ ሠራዊቱ ምንም አይነቱ ተሳትፎም ሆነ እጁ የለበትም ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ እንደሚሉት ፓኪስታን በርካታ መፈንቅለ መንግሥቶችን ያስተናገደችና ለረጅም ጊዜ በቆዩ አምባገነኖች ስትመራ የኖረች አገር መሆኗን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡

XS
SM
MD
LG