በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፔንታገን ለዩክሬን  ጸጥታ የሚውል ተጨማሪ የ300 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ መደበ


በኪየቭ ዩክሬን ወጣ ብሎ ባለና በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ከጥቅም ውጪ የሆነ መኪና ላይ ለመታሰቢያ የተቀመጠ አበባ
በኪየቭ ዩክሬን ወጣ ብሎ ባለና በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ከጥቅም ውጪ የሆነ መኪና ላይ ለመታሰቢያ የተቀመጠ አበባ

የዩናይትድ ስቴትስ የጸጥታ ቢሮ ትላንት አርብ ዋሺንግተን ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረችበት ከየካቲት ወር ማብቂያ ጀምሮ ከመደበችው የ 1.6 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ በተጨማሪ የዩክሬንን ጸጥታ እና ደህንነንት ቢሮ ለመደገፍ የ 300 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ መበጀቱን አስታወቀ፡፡

ይህ ድጋፍም የሌዘር ቴክኖሎጂ፣ የሮኬት መሳሪያዎችን፣ ጢያራዎች፣ ጨለማ ውስጥ የሚያሳዩ መሳሪያዎችን፣ ስልታዊ የመገናኛ ስርዓትን፣ የሕክምና መሳሪያዎች፣ የታጠቁ መኪኖችን እና የጦር መሳሪያዎችን እንደሚያካትት ታውቋል፡፡

የፔንታገን ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ትላንት በሰጡት መግለጫ “ይሄ ውሳኔ የዩናይትድ ስቴትስ ዩክሬን የሩሲያን የጦርነት ምርጫ በማስወገድ አንድነቷን እና የድንበር ሰላሟን ለማስጠበቅ በምታደርጋቸው የጀግንነት ጥረቶች እንደምትደግፋት የማይታጠፍ ቃልኪዳኗን የሚያሳይ ነው ” ብለዋል፡፡

ረቡዕ እለትም የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን እና የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ የዩክሬን ወታደራዊ ሃይልን ለማገዝ ሃይል ጥንካሬን ለማጎልበት መነጋገራቸውን ዋይት ሃውስ አስታውቋል፡፡

በመጋቢት አጋማሽ ኮንግረስ የ13.6 ቢሊየን ዶላር የሰብዓዊን የወታደራዊ ድጋፍ ለዩክሬን እና ምስራቃዊ አውሮፓ የኔቶ አባል ሃገራት የለገሰ ሲሆን ትንሽ ቆይቶም የአንድ ቢሊየን ዶላር የጸጥታ ድጋፍ ለዩክሬን ለገሷል፡፡

እስከዛሬ ድረስ የተለገሰው አብዛኛው ገንዘብም “ፕሬዘዳንታዊ መዋዕለ ንዋይ” ከተሰኘው የሃገሪቱ የመጠባበቂያ ገንዘብ ክምችት የተወሰደ ነው፡፡ ይሁንና ትላንት አርብ ዕለት የተለገሰው የ300 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የፔንታገን የመከላከያ ኢንደስትሪ አጋሮች ለሆኑ የጦር መሳሪያ ወደ ሚያመርቱ አጋሮች ገቢ የሚደረግ ነው፡፡

ትላንት ማምሻውን የፕሬዘዳንት ዘለንስኪን ጥያቄ ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ሶቪየት ሰራሽ ታንኮችን ለዩክሬን እና አጋሮቿ ለማቅረብ እና ለማስተላለፍ መወሰኗን ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናትን ዋቢ ያደረገው የኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ እነዚህ ታንኮች ዩክሬን በምስራቃዊ ዶንባስ ክልል ያሉ የሩስያ ዒላማዎችን እንድትመታ ያግዟታል ብሏል፡፡

ከሳምንታት ግጭት በኋላም ሞስኮ ሩሲያን የሚደግፉ ተገንጣዮች ሁለት ሪፐብሊኮች ያሉባትን ዶኖባስ ነጻነቷን በማስከበሩ ማገዝ ላይ እንደምታተኩር አስታውቃለች፡፡

XS
SM
MD
LG