በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ሶስት የፍልስጤም ታጣቂዎችን በዌስት ባንክ ገደለች


ዌስት ባንክ
ዌስት ባንክ

የእስራኤል የጸጥታ ሃይሎች ሶስት መሳሪያ የታጠቁ የፍልስጤም ጂሃዳዊ ቡድን አባላቶችን በዌስት ባንክ ዛሬ ገደሉ፡፡ ፖሊስ “ይህ የሽብርተኛ ሕዋስ በቅርብ ጊዜ የጸጥታ አባላትን ለማጥቃት በሽብርተኝነት ድርጊት የተሳተፈ ሲሆን ከሰሞኑም ለሌላ ጥቃት እየተዘጋጁ ነበር” ሲል አስታውቋል፡፡

በተልዕኮው አራት የእስራኤል ባለስልጣናት የተጎዱ ሲሆን እስላማዊ ጂሃድ ቡድኑም ሶስቱ ሰዎች አባላቶቹ እንደሆኑ አስታውቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በአረቦች የተፈጸመ ከባድ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ በአካባቢው ውጥረት ነግሷል፡፡ ባለስልጣናትም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ የሆነው የረመዳን የጾም ወቅት መጀምሩን ተከትሎ ጥቃቶች ሊጨምሩ እንደሚችሉ ያስጠነቀቁ ሲሆን ከዚህ ቀደም ግጭቶች በዚህ በረመዳን ወቅት ጨምረው ታይተዋል፡፡

ማክሰኞ ዕለት የፍልስጤም ታጣቂ ተኳሽ ቤኒ ብራክ በተሰኘ አካባቢ 5 ሰዎችን ተኩሶ ከገደለ በኋላ በእስራኤል ፖሊሶች ሊገደል ችሏል፡፡

የእስራኤል ሃይሎችም ሌሎች ሶስት የፍልስጤም ታጣቂዎችን ሃሙስ ዕለት መግደላቸውን ተከትሎ አንድ ፍልስጤማዊ በአውቶቡስ ላይ አንድን ተጓዥ ከጩቤ ከወጋ በኋላ በሌላ እስራኤላዊ ተተኩሶበት የሞተ ሲሆን ይህም የአይሁዶች መኖሪያ በሆነ አካባቢ መፈጸሙ ታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG