የተ.መ.ድ ማሊ ከቡርኪና ፋሶ እና ከኒጀር ጋር የምትጋራው የሶስት ሃገራት የጋራ ድንበር ላይ በሁለት ቡድን የተዋቀረ የሰላም አስከባሪ ቡድን ላከ፡፡
በአካባቢው እራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራው የአሸባሪ ቡድን ጋር ተያያዥነት ባላቸው አካላት ከመጋቢት ወር ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን ባለስልጣናት እና ወታደራዊ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ይህ ቀጠናም በምዕራብ አፍሪካ ከፍተኛ የሆነ ጂሃዳዊ ሚሊሺያ ግጭት የሚካሄድበት ነው፡፡ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስም 500 የሚሆኑ ሲቪሎች ጋኦ እና ሜናካ በተሰኙ አካባቢዎች መገደላቸውን ማንነታቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ወታደራዊ ሃይል አስታውቀዋል፡፡