በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰላም ንግግሩ ቢኖርም ዩክሬኖች ለረጅም ጦርነት እየተዘጋጁ ነው


የሰላም ንግግሩ ቢኖርም ዩክሬኖች ለረጅም ጦርነት እየተዘጋጁ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:37 0:00

የሰላም ንግግሩ ቢኖርም ዩክሬኖች ለረጅም ጦርነት እየተዘጋጁ ነው

በምዕራብ ዩክሬን የሚገኙ የአገሬው ሰዎች የሰላም ድርድሩ በዩክሬንና በሩሲያ መከካል እየተካሄደ ቢሆንም እነሱ ግን ለረጅም ጦርነት እየተዘጋጁ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ሰዎቻቸው በስተጨመጨረሻው በድርድሩ የሚስማሙ ቢሆን እንኳ ለሩሲያ የድንበር መሬት ገምሶ የሚሰጥ የሰላም ድርድር እንደማይቀበሉ ይናገራሉ፡፡

እዚህ ምዕራብ ዩክሬን ውስጥ የምትኘው ተርኖፒል ከተማ፣ በተሰደዱ ቤተሰቦች፣ በእርዳታ ሠራተኞች፣ ምግብ በሚያሰናዱ ሰዎች፣ ልብስ በሚያጥቡና፣ በጦርነቱ ለተጎዱ የአገሬው ሰዎች፣ ሌሎች መሠረታዊ ነገሮችን እያዘጋጁ ከሰላም ድርድሩ ጋር ጦርነቱ አሁንም ወደ ተፋፋመበት ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል በሚልኩ ሰዎች ተሞልታለች፡፡

ብዙዎቹ የሰላም ስምምነት ማለት ለሩሲያ መሬት ገምሶ መስጠት ከሆነ የማይቀበሉ መሆኑን በመግለጽ ለወራት ከዚያም አልፎ በሚዘልቀው ጦርነት ውስጥ በምትገኘው አገራቸው ውስጥ ለመኖር መዘጋጀታቸውን ይናገራሉ፡፡

በተርኖፒል ነዋሪ የሆኑት ኢቫና ሆሺ እንዲህ ይላሉ

"ይህ የሰላም ስምምነት ለዩክሬን መጥፎ በሆነ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አንፈልግም፡፡ እስከ መጨረሻው ድረስ መሬታችንን ነጻ ለማውጣት ዝግጁ ነን፡፡"

የሃይማኖት መሪዎች የአካባቢውን እምነት ያንጸባርቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ ከቤታቸው የተፈናቀሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞችን ጨምሮ፣ ጦርነቱ ከወዲሁ በዩክሬናውያን ተዋጊዮችና ሰላማዊ ሰዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ውድመትና ጉዳት በማሰብ፣ ጦርነት ሊያስከትል በሚችለው ቀውስ ያላቸውን ስጋት ይገልጻሉ፡፡

ዩክሬን ውስጥ በአንድ ወታደራዊ ተቋም ውስጥ ያለ እምነት ተቋም አባት የሆኑት አባ ማይኮላ ኪውዊች እንዲህ ይላሉ

“ጦርነት ቀውስና አውዳሚ ነው፡፡ አሁንም ከተሞቻችንና ሰዎቻችንን ውስጣቸውን እየፈጀ ነው፡፡ ከጦርነት በኋላ እንደ ድሮህ አንድ ዓይነት ሰው ልትሆን አትችልም፡፡”

ምስራቅ ዩክሬን ውስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች ባዶ እየሆኑ በመምጣታቸው እንደ ለቪቭ ያሉ የምዕራብ ከተሞች ከሌላ ቦታ ተሰደው በመጡ ስደተኞች ተጥለቅልቀዋል፡፡ ብዙዎቹ ከሚወዷቸው ተለይተዋል፡፡

ሊውባቫ ተፈናቃይ ከሆኑ አርሶአደር ቤተሰቦች መካከል አንዷ ናቸው፡፡ እንዲህ ብለዋል፡፡

“ሴት ልጄና የልጅ ልጆቼ በስሎቮኪያ ናቸው፡፡ ታላቋ ልጄ በኪዬቭ ናት፡፡ እኔና የልጄ ባለቤት እዚህ ለቪቭ ነን፡፡”

ሊውባቫ ጦርነቱ በቶሎ ያልቃል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ምክንያቱም የአባታቸውን ስም መግለጽ ያልፈለጉት ሊውባቫ እንደሌሎቹ በርካታ አርሶ አደሮች በዚህ ዓመት ለሚያደርጉት የእርሻ ወቅት በቶሎ መዝራት ይፈልጋሉ፡፡

በተርኖፖሊ ያሉት የእርዳታ ሠራተኞች ዩክሬን ምናልባት ከማያባራው ጦርነት ውስጥ ተዘፍቃ ትቀራቸው ብለው ይሰጋሉ፡፡

አንዳንዶቹ በጎ ፈቃደኞች ደግሞ የዩክሬንን መሬት አሳልፎ የመስጠቱን ነገር የማይቀበሉት ቢሆንም አሁንም ቢሆን ግን የሰላም ንግግሩ መቀጠል አለበት ባይ ናቸው፡፡

የሃይማኖት አባት አባ ሮማን ደሙሽ ከእነዚህ አንዱ ናቸው

“ሁሌም መነጋገር ይኖርብናል፡፡ አዋቂ ሰዎች መነጋገር አለባቸው ምክንያቱም ተፈጥሮ ሰዎችን ስታንጸን እንድንነጋገር አድርጋን ነው፡፡ ለዚህ ነው ተኩስ ለማቆም ማናቸውንም ነገር ማድረግ የሚኖርብን፡፡” ብለዋል፡፡

እሳቸው እንደሚሉት መሪዎች ስለሰላም ሲደራደሩ በምድር ላይ ያለው የጥቃት መጠን ይቀንሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ ሌላኛው ካህን የሰላም ድርድሩ የሚገኘው ስምምነት ዋጋ የሚኖረው ስምምነቱን ለመተግባር ሰዎች ቃላቸውን ከጠበቁ ብቻ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG