በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእርዳታ እቃ የጫኑት ተሽከርካሪዎች በቅርቡ መቀሌ ይገባሉ ተባለ


የዓለም ምግብ ድርጅት የእርዳታ እቃ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በቅርቡ መቀሌ ይገባሉ ተባለ
የዓለም ምግብ ድርጅት የእርዳታ እቃ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በቅርቡ መቀሌ ይገባሉ ተባለ

የእርዳታ እቃ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በቅርቡ ወደ መቀሌ እንደሚገቡ የዓለም ምግብ ድርጅት አስታወቀ። የዓለም ምግብ ድርጅት ወደ ትግራይ የላካቸው የእርዳታ እቃ የጫኑ መኪናዎች ወደ ትግራይ መንቀሳቀሳቸውንና ያለምንም እንቅፋት ጉዞ እያደረጉ መሆኑን ድርጅቱ በትዊተር ገፁ ባወጣው መልዕክት አስታውቋል።

ከ500 ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆኑ አስቸኳይ የእርዳታ እቃዎችን የጫኑት መኪናዎች ኢሬፕቲ መድረሳቸውንና ወደ ትግራይ ለመሻገር መቃረባቸውንም ተቋሙ ጨምሮ ገልጿል።

በቅርቡ የእርዳታ ምግብ እና ነዳጅ የጫኑ 23 የጭነት መኪኖች ከሰመራ ተነስተው ጉዞ መጀመራቸውን ያስታወቀው መንግሥት፣ የህወሓት ታጣቂዎች ተኩስ በመክፈት መንገዱን በመዝጋታቸው ምክንያት ከመንገድ መመለሳቸውን መግለጹ ይታወሳል፡፡ ይህን ክስ የማይቀበለው ህወሓት በበኩሉ መኪኖቹ ከሰመራ አለመነሳታቸውን ገልጾ ነበር፡፡

የዓለምድርጅቱ እና አጋር ድርጅቶች ለረሀብ ለተጋለጡ የማኅበረሰቡ ክፍል የሚደርስ ምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦቶች እንደሚገኙበትም አስታውቋል።

"በቅርብ ግዜ ውስጥ መቀሌ እንደርሳለን" ያለው የዓለም ድርጅት፣ ሌላ አንድ ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ የጫኑ መኪናዎች ዛሬ ከሰዓት በኃላ አፋር እንደሚደርስ እና በዳሎል፣ በርሃሌ እና ኮበና የሚገኙ አስቸኳይ ርዳታ ለሚያፈልጋቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደሚከፋፈል ገልጿል። "የእርዳታ አቅርቦቱ ያለምንም ችግር እንዲያልፍም የአፋር ክልል መንግሥት እና ማኅበረሰቡ ድጋፍ እያደረገ ነው" ሲልም የዓለም ድርጅቱ በትዊተር መልዕክቱ አስታውቋል።

20 የዓለም ምግብ ፕሮግራም መኪናዎች ወደ መቀሌ እያመሩ መሆናቸውን አስመልክቶም በትዊተር ገፃቸው ላይ አስተያየት ያሰፈሩት የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ "ይህ ወደ ትክክለኛ አቅጣኛ የሚወስደን ጥሩ እርምጃ ነው። ዋናው ነገር ግን ምን ያክል የጭነት መኪናዎች እንዲሄዱ መፈቀዱ ሳይሆን የሰብዓዊ ርዳታው ሳይስተጓጎል ለተቸገሩት እንዲደርስ ያልተገደበ ሥርዓት ተዘጋጅቷል ወይ የሚለው ነው" ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ትናንት ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 21 ከባድ የጭነት መኪኖች ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸውን ያስታወቀ ሲሆን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ ተሸከርካሪዎቹ ትናንት ከሰመራ ተነስተው በአብዓላ መስመር ጉዞ መጀመራቸውን ተናግረው ነበር፡፡

ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 21 ከባድ የጭነት መኪኖች ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸውን መንግሥት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:34 0:00

አሁንም በአፋር ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት መኖሩን የገለጹት ሚኒስትሩ እርዳታው በአግባቡ እንዲደርስ የህወሓት ታጣቂዎች ከያዟቸው ቦታዎች ለቀው እንዲወጡም በትናንትናው ዕለት አሳስበው ነበር፡፡

በቅርቡ የእርዳታ ምግብ እና ነዳጅ የጫኑ 23 የጭነት መኪኖች ከሰመራ ተነስተው ጉዞ መጀመራቸውን ያስታወቀው መንግሥት፣ የህወሓት ታጣቂዎች ተኩስ በመክፈት መንገዱን በመዝጋታቸው ምክንያት ከመንገድ መመለሳቸውን መግለጹ ይታወሳል፡፡ ይህን ክስ የማይቀበለው ህወሓት በበኩሉ መኪኖቹ ከሰመራ አለመነሳታቸውን ገልጾ ነበር፡፡

XS
SM
MD
LG