በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊ እና ወታደራዊ አጋሮቿ ዓለም አቀፋዊ ግዴታዎቻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

ማሊ እና ወታደራዊ አጋሮቿ ዓለም አቀፋዊ ግዴታዎቻቸውን እንዲወጡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ጥሪ አቀረቡ።

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸኃፊ ጥሪውን ያሰሙት የማሊ የጦር ኃይል በጽንፈኛ እስላማዊ ቡድኖች ላይ በሚያካሂደው ጦርነት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየፈጸመ ነው የሚለው ሥጋት እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት ነው።

ጽንፈኞች ጥቃት እያደረሱ መሆኑን እንደሚገነዘቡ የገለጹት ዋና ጸኃፊው ለፀጥታ ምክር ቤቱ ባደረጉት መግለጫ ማሊ በምታካሂደው ፀረ ሽብርተኛ ዘመቻም በሲቪሉ ህዝብ ላይ ከባድ ጉዳት እየደረሰ ነው ሲሉ ማሳሰባቸውን ኤኤፍፒ ያገኘው መረጃ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG