በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 21 ከባድ የጭነት መኪኖች ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸውን መንግሥት አስታወቀ

ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 21 ከባድ የጭነት መኪኖች ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸውን መንግሥት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:34 0:00

ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 21 ከባድ የጭነት መኪኖች ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸውን መንግሥት አስታወቀ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ ተሸከርካሪዎቹ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከሰመራ ተነስተው በአብዓላ መስመር ጉዞ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

ዛሬም በአፋር ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት መኖሩን የገለጹት ሚስትሩ እርዳታው በአግባቡ እንዲደርስ የህወሓት ታጣቂዎች ከያዟቸው ቦታዎች ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

ግጭቱ ለእርዳታ አቅርቦት መስተጓጎል እንደምክንያት መቅረቡን የሚቃወመው ህወሓት፣ ለተፈጠረው መስተጓጎል መንግሥትን ተጠያቂ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በሌላ ዜና በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጄኮብሰን በመልሶ ማቋቋም እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቶች ድጋፍ ዙሪያ ከአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጋር በሰመራ ተወያይተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG