በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦቦ ገላሳ ዲልቦ


ኦቦ ገላሳ ዲልቦ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:48 0:00

ኦቦ ገላሳ ዲልቦ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የቀድሞ ሊቀ መንበር የነበሩት አቶ ገላሳ ድልቦ ትናንት፤ መጋቢት 21/2014 ዓ.ም. ሌሊት ያረፉት በድንገተኛ የልብ ህመም መሆኑን አንድ የቤተሰባቸው አባል ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ሌሎችም ተቋማትና ታዋቂ ሰዎች ኀዘንናቸውን እየገለፁ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባወጡት መልዕክት “እጅግ በሚያስፈልጉን ጊዜ አጣናቸው” ብለዋል።

አቶ ገላሳ ድልቦ የፓርላማው አባልና የኢንዱስትሪና የማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ሆነው እያገለገሉ እንደነበር ምክር ቤቱ ገልጿል።

የአቶ ገላሳ ድልቦ አስከሬን ሥርዓተ ሽኝት ከነገ በስተያ ቅዳሜ፤ መጋቢት 24 / 2014 ዓ.ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መካነ መቃብር የሚፈፀም መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG