በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍኖተ ሰላም የሚገኙ ተፈናቃዮች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ


ፍኖተ ሰላም ከተማ
ፍኖተ ሰላም ከተማ

ከኦሮምያና ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክሎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች በምግብና በመጠለያ ችግር እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በዞኑ 300ሺ የሚጠጉ ተፈናቃዮች እንዳሉ የሚናገረው የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ችግሩ መኖሩን አምኖ መፍትሔ ለማግኘት ለክልል ማሳወቁን ገልጿል።

የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የምግብ ችግር እጥረት የተከሰተው የፌዴራል አደጋ ሥጋት ኮሚሽን በትራንስፖርት ችግር የእርዳታ እህል በወቅቱ ባለመላኩ ነው ብሏል።

የተፈናቃዮቹን ቅሬታ ለመፍታት የክልሉ መንግሥት ከተለዩ ሴክተሮች የተውጣጡ የባለሞያዎች ቡድን አዋቅሮ ወደ ስፍራው መላኩን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ እያሱ መስፍን ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ፍኖተ ሰላም የሚገኙ ተፈናቃዮች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:23 0:00

XS
SM
MD
LG