በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንክ ለመካከለኛው ምስራቅ አጋሮቻቸው ስለ ኢራን ማረጋገጫ መስጠት ይፈልጋሉ


ብሊንክ ለመካከለኛው ምስራቅ አጋሮቻቸው ስለ ኢራን ማረጋገጫ መስጠት ይፈልጋሉ
please wait
  • Auto
  • 240p
  • 360p
  • 480p
  • 720p

No media source currently available

0:00 0:03:55 0:00
  • Auto
  • 240p
  • 360p
  • 480p
  • 720p

ብሊንክ ለመካከለኛው ምስራቅ አጋሮቻቸው ስለ ኢራን ማረጋገጫ መስጠት ይፈልጋሉ

የዩናዩትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንክን እስራኤልና የባህረ ሰላጤው አገር መሪዎች እኤአ የ2015 የኢራን ኒውክለር ስምምነቱ ቴህራን መቸውም ቢሆን የኒውከለር ጦር መሳሪያው እንዳይኖራት ለመከልከል የተሻለው አማራጭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እስራኤል ጉብኘታቸውን ከጨረሱ በኋላ ብሊንከን ትናንት ማክሰኞ ሞሮኮን ጎብኝተዋል፡፡

ምንም እንኳ ዩናትይት ስቴትስ በአሁኑ ወቅት ትኩረቷን በዩክሬኑ የሩሲያ ወረራ ላይ ያደረገች ቢሆንም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንክን መካከለኛው ምስራቅ ሰሜንና አፍሪካን የሚጎበኝቡት ምክንያት አስረድተዋል

ይህ የዓለም ክፍል የዩናይትድ ስቴትስ ወሳኝ የሆነ ፍላጎት ያለበትና አንዳንድ ወዳጆቻችን ያሉበት ነው፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በክልሉ ኢንቨስት ማድረጓን ከወዳጆቿ ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከሯን ትቀጥልበታለች፡፡ ያ በመካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ መረጋጋትን ለማምጣት ወሳኝ ነው፡፡ ያሉት ፈተናዎች ለመቋቋምና ለውጥ ለማምጣት፣ ለህዝባችን ያሉትን እድሎች ለማስፋት እና እንዲሁም ትኩረታችንን የክሬምሊንን የጦር ተስፋፊነት እንዲያበቃ በማድረጉ ላይ እንድናደርግ ያግዘናል፡፡

ብሊንክን ሞሮኮን የጎበኙት ትናንት ማክሰኞ ሲሆን ከአቡዳቢ አልጋወራሽ ልኡል ጋርም ተገናኝተዋል፡፡ አንድ ባለሙያው ለቪኦኤ እንደተናገሩት በሩሲያው ወረራ የተነሳ በተፈጠረው ቀውስ በተለይ የሰሜን አፍሪካ አገሮች የምጣኔ ሀብት ቀውስ ችግር እንደሚያጋጥማቸው ገልጸዋል፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ተቋም ከፍተኛ ተማራማሪ ራያን ካቱሊስ እንዲ ይላሉ

“እንደሚመለስኝ አንድም የሰሜን አፍሪካ አገሮች እየተወደደ በመጣው የምግብና የነዳጅ ዋጋ የተነሳ ትልቅ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጫናዎች እየደረሱባቸው ይመስለኛል፡፡ የምታስታውስ ከሆነ ህዝባዊ አብዮት ያስነሳው አመጽና አለመረጋጋት የነበረው በቅርቡ ከአስር ዓመት በፊት ነው፡፡ ከዚያ ውስጥ በከፊል ምክንያት የነበረው በወቅቱ በሸቀጦች ዋጋ ላይ የነበረው የዋጋ ውድነት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ በዚህ ረገድ ያለውን ችግር በቅንትጅ ለመከላከል መርዳት የሚቻልበትን ድጋፍ ለመስጠት የሚደረግ ጥቂት የዲፕሎማሲ ስራ ይመስለኛል፡፡”

ብሊንክን በእስራኤል ባደረጉት የመጀመሪያው ጉብኘታቸው ዩናይትድ ስቴትስ ኢራን የኒውክለር ጦር መሳሪያ እንዲኖራት የማትፈቅድ መሆኑን በቀጠናው ላሉት አጋሮቻቸው በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

አሁንም ያን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ሲገልጹ ብሊንከን ይህን ብለዋል

“ዩናይትድ ስቴትስ የጋራ ወደሆነው ሙሉ የድርጊት መርሃ ግብር ለመመለስ የኢራንን የኒውክለር ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዩናይትድ ስቴትስ እንደገና ከዚያ ስምምነት በመውጣቷ ያ ነገር አምልጦ ወጥቷል፡፡”

የባይደን አስተዳደር በኢራን ላይ የተጣለውን ማዕቀብ በማንሳት የ2015 የኢራን ኒውከለር ስምምነትን ወደ ስፍራው ለመመለስ እየሠራ ነው፡፡

ስምንነቱን እኤአ በ2018 የሰረዙት የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነበሩ፡፡

ባለሙያዎች እንደሚሉት በድርድሩ እስካሁን እልባት ካልተሰጠባቸው ነገሮች መካከል ኢራን የአብዮታዊ ዘቧ ከዩናይትድ ስቴትስ የሽብርተኛ ድርጅቶች መዝገብ ውስጥ እንዲወጣ መፈለጓ ነው፡፡

አንድ ባለሙያ እንደሚሉት እስራኤልና ብዙዎቹ የሪፐብሊካን ህግ አውጭዎች ይህን እርምጃ በጽኑ ይቃወማሉ፡፡

ከዲሞክራሲ ጥበቃ ፋውንዴሽን ቤህናም ቤን ታለብሉ እንዲህ ይላሉ

“የባይደን አስተዳደር ይህን ሲፈቅዱ ኒውክለር ስምምነቱን ብቻ ተመልክተው ከሆነ ይህ የኢራንን የሽብርተኝነት መረብ የባለስቲክ ሚሳዬል፣ የክሩዝ ሚሳዬል፣ የድሮን ብቃታቸውን ወይም የተቀረውን ወታደራዊ አቅምና ችሎታቸውን የሚገድብ አይደለም፡፡ ወይም ለዩናይትድ ስቴትስም ሆነ ለአጋሮችዋ በቀጠናው ያለውን የደህንነት ስጋት አያስወገድም፡፡ በኒውክለር ስምምነቱ ብቻ ከኒውከለር ውጭ በሽብርተርኝ ወይም በሚሳዬል ስምምነቱ ሳቢያ የተጣሉትን ማዕቀቦች ማንሳት ትርጉም የሚስጥ ነገር አይደለም፡፡ ግን ምን ያደርጋል አስተዳደሩ የሚሄድበት መንገድና የተከተለው አቅጣጫ በዚያ በኩል ነው፡፡”

ኢራን የኒውከለር ስምምነቱን ማደስ የማይቀር ነው ትላለች፡፡

ባለሙያዎች ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ወደኋላ ተሰንቅረው የቀሩ ብዙ አሳሳቢ ጉዳዮች ስለመኖራቸው ሲናገሩ ከጥንቃቄ ጋር መሆኑንም ይመክራሉ፡፡

XS
SM
MD
LG