በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሃምሳ ዓመት በላይ የሆኑ የኮቪድ ክትባት ማጠናከሪያውን በድጋሚ መከተብ ይችላሉ ተባለ


የሞደርና ክትባት
የሞደርና ክትባት

ዕድሜያቸው ሃምሳ እና ከሃምሳ በላይ የሆኑ ሰዎች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ማጠናከሪያ ክትባት በድጋሚ መከተብ እንዲችሉ የዩናይትድ ስቴትስ የመድሃኒት እና የምግብ አስተዳደር (ኤፍዲኤ) ፈቃድ ሰጥቷል።

ከአሁን ቀደም ሙሉውን ክትባታቸውን ከወሰዱ ሰዎች ውስጥ ማጠናከሪያውን ደግመው እንዲከተቡ የተፈቀደው ከአስራ ሁለት ዓመት ለሆኑ እና የሰውነት የተፈጥሮ የበሽታ መከላከያቸው በከባድ ሁናቴ የተዳከመ ሰዎች ብቻ እንደነበር ይታወሳል።

የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ሲዲሲ ይህ የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር የሰጠው ፈቃድ እንዴት መተግበር እንዳለበት ምክረ ሃሳብ አይሰጥበትም። ሆኖም ኤፍዲኤ ዛሬ ባወጣው መግለጫው ድጋሚ ማጠናከሪያውን ክትባት

ለመውሰድ የሚፈልጉ ሰዎች መከተብ ያለባቸው የቀደመውን ማጠናከሪያ ክትባታቸውን ከወሰዱበት ጊዜ ቢያንስ ከአራት ወር በኋላ መሆን እንዳለበት አሳስቧል።

የዩናይትድ ስቴትስ የመድሃኒት ቁጥጥር አስተዳደር የድጋሚ ማጠናከሪያ ክትባት ፈቃዱን የሰጠው በሀገሪቱ በክረምቱ ወቅት በስፋት ተዛምቶ የነበረው የቫይረሱ ዝርያ አሚክሮን ተጋላጮች ቁጥር እየቀነሰ ባለበት በዚህ ወቅት ነው። ሆኖም ቢኤ2 ተብሎ የተሰየመው አዲስ ዝርያ ዩናይትድ ስቴትስ እና አውሮፓ ውስጥ እየተስፋፋ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከጠቅላላውህዝብ ወደሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የኮቪድ መከላከያ ክትባቱን አሟልቶ ተከትቧል።

ያም ማለት ሁለት የፋይዘር ወይም የሞደርና ክትባት አለዚያ ደግሞ በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቀውን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ክትባት ወስደዋል ማለት ነው። ማጠናከሪያ ክትባት የተከተቡት ደግሞ መከተብ ከሚችሉት ውስጥ ግማሾቹ ብቻ መሆናቸው ተመልክቷል።

ክትባቱ ኦሚክሮን በስፋት እንዳይዛመት ሊከላከል ባይችልም ቫይረሱ ያገኛቸው ሰዎች በጽኑ እንዳይታመሙ ወይም ለህልፈት እንዳይዳርጋቸው ረድቷል።

XS
SM
MD
LG