በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ስምንት ሰላም አስከባሪዎቹ ኮንጎ ውስጥ በደረሰ አደጋ መሞታቸውን አረጋገጠ


ስምንት ሰላም አስከባሪዎችን ይዞ ምስራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ውስጥ ከወደቀው ሄሊኮፕተር አደጋ በህይወት የተረፈ እንደሌለ የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ አስታውቋል።

የፓኪስታን የጦር ሰራዊት አባላት የሆኑ ስድስት የበረራ አባላትን እና አንድ ሰርቢያዊ እና አንድ ሩስያዊ ወታደራዊ አባላትን አሳፍሮ ሰሜን ኪቩ ውስጥ ሲበር መውደቁን ስቴፋን ዱጃሪች ገልጸዋል።

ሰላም አስከባሪዎቹ የተጓዙት ውጊያ የተካሄደበት አካባቢ ሁኔታ ለመከታተል እንደነበር የገለጹት ቃል አቀባዩ ስለአደጋው መነሾ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም፥ በተመለከተ ምርመራ እየተደረገ ነው ብለዋል።

የኮንጎ የጦር ኃይል በበኩሉ ሄሊኮፕተሩን ያን አካባቢ የሚቆጣጠረው ኤም 23 የተባለው አማጺ ቡድን መትቶ ጥሎታል ያለ ሲሆን የቡድኑ ቃል አቀባይ በበኩሉ የጦር ሰራዊቱ የኛ ኃይሎች ላይ ሲተኩስ ሄሊኮፕተሩን መትቶታል ብሏል።

XS
SM
MD
LG