በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት የገባውን ቃል እንዲያከብር ትግራይ ክልል ጠየቀ


ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ
ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ

- መንግሥት የህወሓት ታጣቂዎች የያዟቸውን ቦታዎች መልቀቅ አለባቸው ብሏል

የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ሲባል ግጭት በማቆም የተናጥል የተኩስ ማቆም ውሳኔውን ይፋ ቢያደርግም እስካሁን ግን ወደ ትግራይ ክልል የገባ ምንም ዓይነት እርዳታ እንደሌለ የትግራይ ክልል መንግሥት አስታወቀ።

በሌላ በኩል እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል መግባት እንዲችል የህወሓት ታጣቂዎች ከያዟቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው መውጣት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት አስቸኳይ የሰብዓዊ አቅቦቶችን ወደ ትግራይ ክልል ለማድረስ የተናጥል የተኩስ ማቆም ለማድረግ መወሰኑን ሐሙስ መጋቢት 15/2014 ዓ.ም አስታውቆ የነበረ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ የትግራይ ክልል መንግሥት ግጭቱን በአስቸኳይ ለማቆም መወሰኑን አስታውቋል።

የትግራይ ክልልን በመወከል አስተያየት የሰጡን ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ህይወት ይህን ሥምምነት ከተደረገ በኋላ ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ተከታታይ ሦስት ቀናት ወደ ክልሉ የገባ ምንም ዓይነት የሰብዓዊ ድጋፍ የለም ብለዋል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ፣ መንግሥት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ከወሰነ በኋላ፣ የህወሓት ታጣቂዎች በኃይል ከያዟቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ባለመውጣታቸው እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል መሔድ እንዳልቻለ ገልጸዋል፡፡

በትናንትናው ዕለት ህወሓት ከያዛቸው የአፋር ክልል ወረዳዎች በአንዱ ውጊያ ሲደረግ እንደዋለም ተናግረዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ መንግሥት የገባውን ቃል እንዲያከብር ትግራይ ክልል ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:34 0:00

XS
SM
MD
LG