በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሊባን የአሜሪካ ድምፅ እና የቢቢሲ የዜና ፕሮግራሞችን አገደ


በአፍጋኒስታን የግል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች የአሜሪካ ድምፅን እና የቢቢሲን የዜና ፕሮግራሞች እንዳያስተላልፉ ታሊባን መከልከሉ ተገለጸ።

አክራሪ እስላማዊው ታሊባን ባለፈው ነሃሴ ወር የመንግሥት ሥልጣን ከያዘ ወዲህ የመናገር ነጻነትን የማፈን እርምጃውን ቀጥሏል። የአሜሪካ ድምፅ ታሊባንን ስለወሰደው እርምጃ ፈጥኖ አውግዟል።

የአሜሪካ ድምፅ ዳይሬክተር ዮላንዳ ሎፔዝ ትናንት ባወጡት መግለጫ ታሊባንይህን አሳዛኝ እርምጃ እንዲቀለብስ እንጠይቃለን ብለው ታሊባን የሥርጭት ይዘቶችን ለመገደብ የሚያደርጋቸው ሙከራዎች የአፍጋኒስታን ህዝብ የሚገባውን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ጋር በቀጥታ የሚቃረን ነው ብለዋል።

በአፍጋኒስታን የግል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች የአሜሪካ ድምፅ እና የቢቢሲ የዜና ፕሮግራሞች እንዳያስተላልፉ ታሊባን መከልከሉ ተገለጸ።

XS
SM
MD
LG