በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡርኪና ፋሶ ድንበር አቅራቢያ 6 የኒጀር ወታደሮች ተገደሉ


በጅሃዲስቶች ጥቃት ከቡርኪና ፋሶ ወደ አይቮሪኮስት ለመሰደደ የተገደዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መጠለያ ካምፕ እኤአ ጥር 2022 ቱጎቦ (ፍቶ ፋይል)
በጅሃዲስቶች ጥቃት ከቡርኪና ፋሶ ወደ አይቮሪኮስት ለመሰደደ የተገደዱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መጠለያ ካምፕ እኤአ ጥር 2022 ቱጎቦ (ፍቶ ፋይል)

ኒጀር ደቡባዊ ምዕራብ ግዛት በቡርኪና ፋሶ ድንበር አቅራቢያ ጅሃዲሶቶች ባደረሱት ጥቃት 6 ወታደሮች መገደላቸውን የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ትናንት ቅዳሜ አስታውቋል፡፡

ባላፈው ሀሙስ የተፈጸመው ጥቃት በአስር ቀናት ውስጥ ሁለተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አደጋው የደረሰው እኤአ ከ2017 ጀምሮ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ጅሃዲስቶች በሚንቀሳቀሱበት የቡርኪና ፋሶ፣ የማሊና የኒጀር ድንበርን በሚሸፍነው አካባቢ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ባለፈው ሳምንትም ጅሃዲሶቶቹ በተመሳሳይ ስፍራ ባንድ የህዝብ ማመለላሻ አውቶብሳ ላይ ባደረሱት ጥቃት 21 ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸው ተነገሯል፡፡

የኒጀር ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ባዙም ሰላም ለማውረድ በሚቻልበት ሁኔታ ከጅሃዲስቶች ጋር ለመነጋገር አዲስ የተነሳሽነት ጥረት መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ 1ሺ400 ኪሜትር በሚሸፍነው በማሊና ቡርኪና ፋሶ ድንበር አካባቢ 12 ሺ ወታደሮችን በማሰማራት ጅሃዲስቶችን የማጥቃት እንቅስቃሴም እየተካሄደ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG