በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘለንስኪ ለዶሃ ዓለምቀፍ ጉባኤ ተሳታፊዎች ንግግር አደረጉ


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ትናንት ቅዳሜ በዶሃ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ያልተጠበቀ የቪድዮ ንግግር አሰምተዋል፡፡ እኤአ መጋቢት 26
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ትናንት ቅዳሜ በዶሃ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ያልተጠበቀ የቪድዮ ንግግር አሰምተዋል፡፡ እኤአ መጋቢት 26

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ትናንት ቅዳሜ በዶሃ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ባሰሙት ያልተጠበቀ የቪድዮ ንግግራቸው ነዳጅ አምራች አገሮችና ሌሎች አገሮች የሩሲያን የኃይል አቅርቦት የሚተካ ተጨማሪ የምርት እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡

እኤአ ከየካቲት 24 ጀምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍል ተማጽኗቸውን ሲያሰሙ የቆዩት ዘለንስኪ፣ በዶሃ ንግግራቸው፣ ሩሲያ በማሪዩፖል የምታደርሰውን ውድመት ሩሲያና ሶሪያ በሶሪያው ጦርነት በአሌፖ ላይ ካደረሱት ውድመት ጋር አመሳስለውታል፡፡

ዘለንስኪ በንግግራቸው፣ “ወደቦቻችንን እያወደሙ ነው፡፡ ከዩክሬን ምንም ነገር አይላክም ማለት በመላው ዓለም ለሚገኙ አገሮች ትልቅ አደጋ ነው” ብለዋል፡፡

ከዩክሬን የሚላከው ስንዴ በመከካለኛው ምስራቅ እንደ ግብጽ ባሉ አገሮች ላይ ከወዲሁ ከፍተኛ ችግር እያስከተለ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ዘለንስኪ በተለይ በዓለም ላይ የተፈጥሮ ጋዝ በማምረት ቀዳሚነትን የያዘቸው ኳታርን ጨምሮ አገሮች ምርታቸውን ከፍ በማድረግ የሩሲያን ተጽእኖ እንዲገቱ አሳሰባዋል፡፡

XS
SM
MD
LG