በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መልዕክተኛው የኢራን የኒውክለር ስምምነት ስለመሳካቱ እምነት የለኝም አሉ


የዩናይትድ ስቴትስ የኢራን ልዩ መልዕክተኛ ሮበርት ማሊ (ፎቶ ፋይል)
የዩናይትድ ስቴትስ የኢራን ልዩ መልዕክተኛ ሮበርት ማሊ (ፎቶ ፋይል)

የኢራን የኒውክለር ስምምነት ተግባራዊ ስለመሆኑ እርግጠኛ አለመሆናቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የኢራን ልዩ መልዕክተኛ ሮበርት ማሊ ዛሬ እሁድ በሰጡት መግለጫ ተናገሩ፡፡

ማሊ በዶሃ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ሲናገሩ “ከጥቂት ወራት በፊት ስምምነቱን ለመቋጨት በጣም የተቃረብን መስሎኝ ነበር ... አሁን ግን ብዙም እምነት የለኝም” ብለዋል፡፡

የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ካሚኒ ከፍተኛ አማካሪ ከማል ካኽራዚ ኮንፈረሱ ላይ ሲናገሩ ስምምነቱ በቅርቡ እልባት ማግኘቱ የማይቀር መሆኑን ገልጸው ይሁን እንጂ በዩናይትድ ስቴትስ የፖለቲካ ፈቃደኝነት የሚወሰን ነው ብለዋል፡፡

በዓለም ኃያላን አገሮችና ኢራን መካከል ለ11 ወራት በቪያና ሲካሄድ የቆየው ስምምነት አለመሳካቱ በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረትን ሊያባብስ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG