በኦሮምያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከተከሰተው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘው ከ700 ሺሕ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸዉ መፈናቀላቸውን የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኦሮምያ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር አቶ ገረሙ ኦሊቃ ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑት የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። ኮሚሽኑም ድጋፎችን እያቀረበ መሆኑን ገልፀዋል። ሁለቱ የጉጂ ዞኖችና ምዕራብ ኦሮምያ ዞኖች በከፍተኛ ሁኔታ ሰዎች የተፈናቀሉባቸው መሆኑን አቶ ገረሙ ተናግረዋል።
የክልሉ ፀጥታ ጉዳይ በኦሮምያ ክልል ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አብይ ርዕስ የነበረ ሲሆን፣ የክልሉ የፀጥታና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሻፊ ሁሴን፣ የክልሉ መንግሥት የክልሉን ፀጥታ ወደ ቦታው ለመመለስ እየሠራ መሆኑን ለአባላቱ ተናግረዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።