በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፈተና አስተራረም አካል ጉዳተኞች የበለጠ ተጎጂ ናቸው ተባለ


ፎቶ ፋይል፦ ደሴ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ ደሴ ከተማ

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂ ብሔራዊ ፈተና አስተራረምና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አካል ጉዳተኞች ተጎጂ መሆናቸውን የአማራ ክልል አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

በተለይ ዓይነ ስውራንና መስማት የተሳናቸው ተፈታኞች ዝቅተኛ ውጤት ማምጣታቸውን የሚናገረው ፌዴሬሽኑ በጦርነቱ ምክንያት በቂ ዝግጅት አለማድረጋቸውንና ፈተናውን ሲወስዱ በተረጋጋ የሥነ ልቦና አቋም ውስጥ አለመገኘታቸውን እንደ ምክንያት ያቀርባል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤቱ ይሄን ግምት ውስጥ ያላስገባ በመሆኑ በተፈታኞች ሞራል ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩን የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ፍሬሰላም ዘገዬ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል አስተራረሙና የውጤት አሰጣጡ ደረጃውን አልጠበቀም ስህተትም አለበት የሚሉ በደሴ የሚኖሩ ዓይነ ስውራን ተፈታኞች ውጤቱን እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በፈተና አስተራረም አካል ጉዳተኞች የበለጠ ተጎጂ ናቸው ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:20 0:00

XS
SM
MD
LG