በኢትዮጵያ የኦጋዴን ተፋሰስ ያለውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ መጠን እና ኢኮኖሚያዊ ግምገማን የሚያሳይ ጥናት ለማድረግ በአሜሪካ ኩባንያና በማዕድን ሚኒስቴር መካከል ሥምምነት ተፈጸመ።
በሥምምነት ሥነ ስርዓቱ ላይ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጄኮብሰን የተገኙ ሲሆን፣ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ ያለው ጥናት እንዲደረግ ከማስቻል ባለፈ በሃገራቱ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንደሚያጠናክርም ተገልጿል፡፡