በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዝቋላ ወረዳ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፋናቃዮች አስቸኳይ እርዳታ እንዲሰጣቸው ጠየቁ


በዝቋላ ወረዳ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፋናቃዮች አስቸኳይ እርዳታ እንዲሰጣቸው ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:08 0:00

በዝቋላ ወረዳ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፋናቃዮች አስቸኳይ እርዳታ እንዲሰጣቸው ጠየቁ

በአማራ ክልል ዋግህምራ ዞን ከስድስት ቀበሌዎች ተፈናቅለው በዝቋላ ወረዳ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ከ18ሺ በላይ ተፈናቃዩች ለከፋ የረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች ተናገሩ።

ተፈናቃዮቹ እንደሚሉት በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ከሦስት ወራት በላይ ቢቆዩም በቂ ምግብ ማግኘት ባለመቻላቸው በተለይ ህፃናት ከምግብ እጥረት የሚመጣ በሽታ እያጠቃቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የዝቋላ ወረዳ የጤና ጽሕፈት ቤት ተወካይ ኃላፊ አቶ እስጢፋኖስ ወልዴ በምግብ እጥረት ምክንያት የታመሙ 12 ሕፃናት ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቁመው ችግሩ ትኩረት ካልተሰጠው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በበኩሉ አሁንም በህወሓት ቁጥጥር ስር ካሉ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያና በሌሎች አካባቢዎች ከ61ሺሕ በላይ ተፈናቃዩች እንደሚገኙ አስታውቋል።

ለተፈናቃዮቹም በቂ የምግብ እርዳታ እየተላከ መሆኑን ኮሚሽነር ዘላለም ልጅለም ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG