በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትናንት ከወደቀው የቻይና ቦይንግ አውሮፕላን የተረፉ ሰዎች ፍለጋ ቀጥሏል


በቻይና ጉዋንግዚ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ከተከሰከሰበት ሥፍራ አቅራቢያ አንዲት ሴት በቡድሃ እምነት ለተጎጂዎች መታሰቢያ ሲያደርጉ እአአ መጋቢት 22/2022
በቻይና ጉዋንግዚ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ከተከሰከሰበት ሥፍራ አቅራቢያ አንዲት ሴት በቡድሃ እምነት ለተጎጂዎች መታሰቢያ ሲያደርጉ እአአ መጋቢት 22/2022

ትንናት ሰኞ በቻይና ደቡባዊ ክፍለ ግዛት ጉዋንግዚ፣ በውዙ ከተማ ወድቆ መከስከሱ የተነገረውን የቻይና ኢስተርን አየር መንገድ ቦይንግ ጀት አውሮፕላን ስብርባሪ መገኘቱ የተገለጸ ሲሆን በህይወት የተረፉ ካሉ ለማወቅ አሰሳው መቀጠሉ ተነግሯል፡፡

የቻይና መገናኛ ብዙሃን በአካባቢው የአደጋ ጊዜ አሳሾች ከአውሮፕላኑ ስብርባሪው ውስጥ በህይወት ወድቆ የተገኘ ሰው አለማግኝታቸውን አስታውቀዋል፡፡

አደጋው በደረሰበት ወቅት የቦይንግ 737 አውሮፕላኑ 123 መንገደኞችና 9 የአየር መንገድ ሠራተኞችን አሳፍሮ በምዕራብ ቻይና ከምትገኘው ከንሚንግ ከተማ፣ በምስራቅ ወደ ምትገኘው ጉዋንጉዚ ከተማ ይበር እንደነበር ተመልክቷል፡፡

በአደጋው አካባቢ በነበረው አሰሳ የተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች ከሌሎች አገሮች ቤተሰቦቻቸውን ፍለጋ ወደ ሥፍራ ለመጡ ሰዎች መረጃዎችን ሲያቀብሉ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG