በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዘይት እጥረትና የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ምሬት


የዘይት እጥረትና የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ምሬት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:42 0:00

የዘይት እጥረትና የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ምሬት

የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች በከተማዋ በተከሰተው የዘይት እጥረትና የዋጋ ውድነት መማረራቸውን ገለጹ። “በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ የሚቀርበው ዘይትም በአግባቡ ለተቸገሩት እየደረሰ አይደለም” ሲሉ ተጠቃሚዎች ቅሬታቸውን ገልጸዋል። በመንግሥት ኮታ ወጥቶለት ከሸሙ ዘይት ፋብሪካ ለከተማዋ ነዋሪዎች የሚከፋፈለው የዘይት መጠን በ2/3ኛ መቀነሱ ዋነኛ የችግሩ ምንጭ መሆኑን የከተማዋ አስተዳደር አስታውቋል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በዓለም ገበያ የምግብ ዘይት ዋጋ መናር እና የሕጋዊና ሕገወጥ ነጋዴዎች አሉታዊ ሚና ለዋጋ ጭማሪው የራሱን አስተዋፅዖ ማበርከቱን ገልጿል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ 150 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በመጪዎቹ ሦስት ወራት ሊገዛ መወሰኑን ባለፈው ሳምንት ማስታወቃቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG