በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተ.መ.ድ እምባ ጠባቂ ተቋም የደቡብ ሱዳን ምርጫ ወደ ብጥብጥ ሊያመራ ይችላል ሲል አስጠነቀቀ


South Sudanese refugees receive food after being transported from the border of South Sudan and the Democratic Republic of the Congo (DRC) to a refugee settlement site in Aru, DRC, May 10, 2019.
South Sudanese refugees receive food after being transported from the border of South Sudan and the Democratic Republic of the Congo (DRC) to a refugee settlement site in Aru, DRC, May 10, 2019.

የተ.መ. ድ እምባ ጠባቂ ተቋም የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግስት በሕገ መንግስቱ መሰረት የተቀመጠውን እና በአጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ያለውን የሰላም ስምምነት ተፈጻሚ ማድረግ ሳይችል ወደ ምርጫ ሂደት ከገባ ሃገሪቱ ከባድ ወደ ሆነ ብጥብጥ ትገባለች ሲል አስጠነቀቀ፡፡

ደቡብ ሱዳን በመጪው እ.ኤ.አ 2023 ብሔራዊ ምርጫ እንደሚኖራት ይጠበቃል፡፡ ይሁንና የሃገሪቱን ላለፉት ሶስት ዓመታት በሽግግር መንግስትነት ሲያስተዳደር የቆየው መንግስት የእርስ በርስ ጦርነት ያስቆመውን የሰላም ስምምነት አተገባበሩ ግን ሲተች ቆይቷል፡፡

የደቡብ ሱዳን የኮሚሽን አባላት በሰላም ስምምነቱ ውስጥ ቁልፍ የሆኑ ነገሮች ተፈጻሚ ሳይሆኑ ቆይተዋል ሲሉ ይከሳሉ፡፡ በዋናነትም ብጥብጥ መቀጠል፣ በስርዓቱ የሚደገፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ነጻና ፍትሃዊ የሆነ ምርጫ ለማካሄድ ጋሬጣ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ሊቀንበር ያስሚን ሱቃ ግጭቱ 4 ሚሊየን ሰዎችን በሃገር ውስጥ እና በጎረቤት ሃገራት እንዲሰደድ አድርጓል ይላሉ፡፡ ሊቀመንበሯ 9 ሚሊየን የሚደርሱ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ይሻሉም ይላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መንግስት በፖለቲካ ልሂቃን በሃገሪቱ ግምጃ ቤት ላይ እያደርሱ ያለው ሙስና እንቆቅልሽ ሆነበታል የሚሉ ሲሆን ጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ እና በዘፈቀደ የሚፈጸም እስር እየተሰቃዩ ነው ይላሉ፡፡ ሊቀምበሯ አያይዘውም በደቡብ ሱዳን ስልታዊ በሆነ ሁኔታ ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ጾታዊ ጥቃት እየደረሰ ነው ይላሉ፡፡ ይህ ተከትሎም ምርጫ ማካሄዱ ከባድ ፈተናዎች እንዳሉት አስረድተዋል፡፡

“በዚህ የፍርሃት እና የሽብር ድባብ በነገሰበት ሁኔታ እንዴት ሕገመንግስት ስለመመስረት፣ ስለምርጫ እና የሽግግር የፍትህ ስርዓት ስለማቋቋም ማውራት የሚቻለው እንዴት ነው? ለመሆኑ ብሄራዊ ምክክርስ ማድረግ ይቻላል ወይ? እያደገ የመጣው የፖለቲካ ቀውስ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ እና የሰብዓዊ መብት ችግር በማባባስ ”የአብዛኞቹን ደቡብ ሱዳናዊያን ሕይወት የማይቻል አድርጎታል፡፡”

የኮሚሽኑ አባል የሆኑት አንድሩ ካልፋም የሕገ መንግስቱ ቁልፍ ነገሮች ላይ ስምምነት አልተደረሰም ይላሉ፡፡ ሕገመንግስቱን ማዘጋጀት እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ስምምነት ያሻል ሲሉም ያሳስባሉ፡፡

“ሕጋዊ እና አካሄድን ከተመለከቱ ቁልፍ ነገሮች ባሻገር፤ ሂደቱን በተመለከተ በቂ የሆነ የመሰረት ስራ ባልተሰራበት ሁኔታ ውስጥ በዚህ ምርጫ ውስጥ ተጨማሪ ክፍፍልን እና ብጥብጥን የሚፈጥር አደጋ እንዳለ ልብ ማለት ያሻል፡፡ የተረጋገጠ ሰላም እና ዴሞክራሲያዊ ሁኔታዎች ባለተመቻቹበት ወደ ተቻኮለ ምርጫ ማምራት የሚያስከትለው ውጤት በእርግጥም አደገኛ ነው የሚሆነው፡፡”

XS
SM
MD
LG