በአውሮፓ ኖርዌይ በኔቶ ስር ሆኖ ወታደራዊ የጦር ልምድድ ሲያደርግ በነበረው አንድ ዩናይትድ ስቴትስ የጦር አውሮፕላን ላይ ትናንት ዓርብ በደረሰ አደጋ በውስጡ የነበሩ የአራት አሜሪካውያን ህይወት ማለፉ ተነገረ፡፡
የአካባቢዎ ፖሊሶች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አደጋው በደረሰበት የጦር አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ሁሉም ህይወታቸው ማለፉን ገልጸው አራቱም የአሜሪካ ዜግነት የነበራቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡
የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጆነስ ጋኻር ባስተላለፉት የትዊት መልዕክት በአራቱ አሜሪካውያን ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡
የአደጋው መንስኤ እየተጠና ሲሆን በአስቸጋሪው የአየር ጠባይ የተነሳ በተፈለገው ፍጥነት ማካሄድ አለመቻሉም ተመልክቷል፡፡
ኖርዌን ለመከላከል በሚደረገውና ኮልድ ሪስፖንስ የሚል ስያሜ በተሰጠው የኔቶ ጦር ልምድድ፣ ከ27 አገሮች የተውጣጡ ወደ 30ሺ ወታደሮች መሳተፋቸው ተነግሯል፡፡