በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኢትዮጵያውያን ወላጆቹ የተወለደው ግርማይ ዛሕለይ በሲያትል የኪንግ ካውንቲ ምርጫ አሸነፈ


የ32 ዓመቱ የሕግ ባለሞያ ግርማይ ዛሕለይ
የ32 ዓመቱ የሕግ ባለሞያ ግርማይ ዛሕለይ

ከኢትዮጵያውያን ወላጆቹ የተወለደው የ32 ዓመቱ የሕግ ባለሞያ ግርማይ ዛሕለይ በሲያትል የኪንግ ካውንቲ ምርጫ አሸነፈ። ባለፈው ማክሰኞ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለተካሄደው ምርጫ ሲያትል ከተማ ለምትገኝበት የዋሽንግተን ግዛት ኪንግ ካውንቲ ምክር ቤት አባልነት ተወዳድሮ ያሸነፈው ግርማይ አሁን ለደረሰበት ከፍ ያለ ቦታ የበቃው “እናቴ በከፈለችው መስዋትነት ነው” ሲል በመግለፅም እናቱን አመስግኗቸዋል።

እናቱ ወ/ሮ አበባ አናጋው “ሁለት ሥራ እየሠራሁ ያሳደኩት ልጄ እዚህ በመድረሱ ደስታዬ ወደር የለውም" ብለዋል።

/ጽዮን ግርማ ግርማይ ዛሕለይ እና እናቱን ወ/ሮ አበባ አናጋውን አነጋግራ ያሰናዳችውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

ከኢትዮጵያውያን ወላጆቹ የተወለደው ግርማይ ዛሕለይ በሲያትል የኪንግ ካውንቲ ምርጫ አሸነፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:39 0:00

XS
SM
MD
LG