የኢትዮጵያ መንግሥት የሕግ ማስከበር ዘመቻ ያለውን ባካሄደበት ወቅት፣ በሀገሪቱ ላይ የተሰነዘረውን ዓለም አቀፍ ጫና በማቃለል ቻይና ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር አስታወቀ።
በሳዑዲ አረቢያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል 35 ሺህ የሚሆኑት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ መመዝገባቸውንም የሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።
ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በበኩላቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ገልፀዋል።