ስድስት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ስምንት ግለሰቦች የቀድሞ ተማሪዎቹ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ።
በአሁኑ ሰዓት የመማር ማስተማር ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ እየተከናወነ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት የኮምዩኒኬሽንስ አማካሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ሆኖም በሥጋት ምክንያት ብዙ ተማሪዎች ይህ ዘገባ ዛሬ /ረቡዕ/ እስከተጠናቀረ ድረስ ወደ ማደሪያቸው አለመመለሳቸውን አስተያየቻውን ለቪኦኤ የሰጡ ተማሪዎች ገልፀዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።