በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የለገሰችው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ 7.8 ሚሊዮን ደረሰ


የኮቪድ-19 ክትባት
የኮቪድ-19 ክትባት

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በዓለም ዙሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመዋጋት በያዘው ጥረት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 840 ሺህ ስድሳ ነጠላ የፋይዘር ክትባቶችን መለገሷን በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስታውቋል።

ተጨማሪው የክትባት ድጋፍ ዩናይትድ ስቴትስ ለዓለም ሀገሮች ከመደበችው የክትባት እርዳታ ውስጥ ሃያ አምስት ሚሊዮኑን ለአፍሪካ ሀገሮች ለመለገስ በገባችው ቃል መሰረት መሆኑን መግለጫው ጠቅሷል።

ክትባቶቹን ደህንነቱ በተጠበቀ እና በፍትሃዊነት የምናጋራው ከሌላ አንዳችም ጉዳይ ጋር ሳይያያዝ የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ባለን ዓላማ ብቻ ነው ሲል ኢምባሲው አክሎ ገልጿል።

የኮቪድ ክትባቶች በፍትሃዊ መንገድ እንዲዳደረሱ በሚሰራው በኮቫክስ አማካይነት ከትናንት በስተያ ሰኞ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ከደረሰው የኋለኛው ድጋፍ ጋር ዩናይትድ ስቴትስ እአአ ካለፈው ዓመት ሃምሌ ወር ወዲህ ለኢትዮጵያ የለገሰችው ክትባት ቁጥር ከሰባት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG