በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከደቡብ ሱዳን ድንበር የተፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑን ጋምቤላ ክልል አስታወቀ


ጋምቤላ ከተማ
ጋምቤላ ከተማ

ደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ ተከስቷል በተባለው ግጭት የተፈናቀሉት ከ9 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት አቶ ኡጌቱ አዲንግ “በደቡብ ሱዳን ኃይሎችና ኤስ.ፒ.ኤል. ኤም- አይ ኦ በተባሉ ታጣቂዎች መካከል ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የካቲት 29/2014 ዓ.ም በተቀሰቀሰ ግጭት ሳቢያ በድንበር አካባቢ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል አንድ ሰው ሞቷል፣ ስድስት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል" ብለዋል።

ከደቡብ ሱዳን ድንበር የተፈናቀሉት ኢትዮጵያውያን ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑን ጋምቤላ ክልል አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:18 0:00

ከዚያ በኋላም ነዋሪዎቹ ቀያቸውን ጥለው መፈናቀላቸንና ገልፀው የነዋሪዎቹን ምግብን ጨምሮ ንብረቶቻቸው በመዘረፉ መልሶ ለማቋቋም እና ወደ ቀያቸው ለመመለስ መንግሥት መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ድጋፍ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ ዙርያ ከደቡብ ሱዳን መንግሥትም ሆነ ከታጣቂዎቹ እስከ አሁን የተሰማ ነገር የለም።

የአሜሪካ ድምፅ የደቡብ ሱዳን የመከላከያ ኃይሎች ቃል አቀባይ ጀነራል ሉል ሩአኢ ኮአንግ በስልክ ለማግኘት ከትናንት ጀምሮ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

XS
SM
MD
LG