በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማሮ ወረዳ ግጭትና የ“ኮሬ” ማኅበረሰብ አቤቱታ


የአማሮ ወረዳ ግጭትና የ“ኮሬ” ማኅበረሰብ አቤቱታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:26 0:00

የአማሮ ወረዳ ግጭትና የ“ኮሬ” ማኅበረሰብ አቤቱታ

በደቡብ ክልል የአማሮ ወረዳ ነዋሪዎች እነርሱ “ሸኔ” እያሉ በሚጠሯቸው ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ገለፁ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የውሃ መስኖ እና የአርብቶ አደሮች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የዶ/ር አወቀ አምዛዬ፤ በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ታጥቀው መሽገዋል ያሏቸው ታጣቂ ቡድኖች “በአማሮ ወረዳ በሚገኙ ኮሬ ብሔረሰብ ላይ የዘር ማጥፋት እየፈፀሙ ነው” ሲሉ ይከሳሉ። አያይዘው “የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም ሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን በዝምታ አልፎታል” ብለዋል።

የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በበኩላቸው “የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመ ነው የሚባለው በአንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲፈፀም ነው ፤በኦሮምያ ክልል ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው ቡድን ጥቃት እያደረሰ ያለው በኦሮም ህዝብ ላይም ጭምር ነው” ብለዋል። በዚህም ምክኒያት ጉዳዩን የዘር ማጥፋት ነው ማለት እንደማይቻል ተናግረዋል። “ይህንን ለመከላከል ደግሞ መንግሥት እርምጃ እየወሰደ ነው” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በበኩላቸው በኢትዮጵያ ቁጥራቸው የበዙ ብሔረሰቦች ተመሳሳይ አቤቱታ እንደሚያቀረቡ ጠቁመው ሁሉም ጋር ደርሶ ለመርመር እና ለማጣራት ኮሚሽኑ የአቅም ውስንነት እንዳለበት ተናግረዋል። አያይዘውም ሁሉንም ጥቃት ግን «የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው» እያሉ መክሰስ ከዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችና ሕግ አኳያ ተገቢነት እንደሌለው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ አቶ ኦዳ ተርቢ ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ድምፅ ስለ ተመሳሳይ ጥቃቶች ተጠይቀው የእነርሱ ታጣቂዎች የመንግሥት ወታደሮችን እንጂ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ እንደማያደርጉ በመግለፅ አስተባብለው ነበር።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአማሮ ልዩ ወረዳና በኦሮምያ ክልል የገላና ወረዳ ነዋሪዎች የመንግሥቱ ባለሥልጣናት “ኦነግ ሸኔ” የሚላቸው፣ እራሳቸውን “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” ብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች ያደርሱብናል የሚሏቸው ጥቃቶች እየተባባሱ መምጣታቸውን ሰሞኑን ለአሜሪካ ድምፅ መናገራቸውን ሰሞኑን መዘገባችን ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG