በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ጉዳይ የብልፅግና ውሳኔና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምላሽ


ፎቶ ፋይል፦ የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ
ፎቶ ፋይል፦ የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ

የትግራይን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ብልፅግና ፓርቲ ያሳለፈውን ውሳኔ ቢደግፉም፣ በተግባራዊነቱ እና በሂደቱ ላይ ጥያቄ እንዳላቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ገለጹ።

ቀድሞውንም ጦርነት ውስጥ የተገባበት መንገድ ስህተት እንደነበር የሚገልጹት የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ አሁንም ቢሆን ሰላማዊ መፍትሔ በትኩረት ሊተገበር ይገባል ብለዋል፡፡

የአረና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋይ ደግሞ፣ ውሳኔው በፍጥነት እንዲተገበር ጠይቀው፣ ነገር ግን በተግባራዊነቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው አንስተዋል፡፡

የኢዜማ የድርጅት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ደግሞ፣ የብልፅግናን ውሳኔ ቢደግፉም የጦርነቱ ውጤት ሳይታወቅ ተደርጓል ያሉትን የአቋም ለውጥ እንደማይቀበሉ ተናግረዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ፣ የትግራይ ሕዝብ ችግሮችን ለመፍታት አሉ የተባሉ የሰላም አማራጮችን ሁሉ እንደሚጠቀም ማስታወቁን በመጥቀስ፣ የትግራይ ክልልን በማስተዳደር ላይ ያለውን መንግሥት ምላሽ የጠየቅናቸው በውጭ ሀገራት የትግራይን ክልልን ወክሎ የሚንቀሳቀሰው ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ዮሃንስ አብርሃ የሰጡት ምላሽም በዘገባው ተካቷል።

በትግራይ ጉዳይ የብልፅግና ውሳኔና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:33 0:00

XS
SM
MD
LG