በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራና አፋር ክልል የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችና የጦርነት ወንጀሎች መፈፀማቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ


በአማራና አፋር ክልል የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችና የጦርነት ወንጀሎች መፈፀማቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:08 0:00

በአማራና አፋር ክልል የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችና የጦርነት ወንጀሎች መፈፀማቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

በአማራና በአፋር ክልል የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችና የጦርነት ወንጀሎች መፈፀማቸውን በምርመራው ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ይፋ አደረገ። የትግራይ ተዋጊዎች ወሲባዊና የፆታ ጥቃትን የጦርነት ዓላማቸው ለማራመጃ እንደተጠቀሙበት ጠንካራ ማስረጃዎችን እንዳሉት ኮሚሽኑ አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በሁለቱ ክልሎች ምርመራ ባደረገባቸው ስፍራዎች ሆነ ተብለው የተፈፀሙ ግድያዎችን ሳይጨምር በጦርነቱ ውስጥ በሲቪል ሰዎች የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን አስታውቋል። የምርመራ ግኝቱ ሪፖርት በተደረገበት በዛሬው ዕለት መግለጫ የሰጡት ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ፤ “ቢያንስ 403 ሲቪል ሰዎች ለሞት እንዲሁም 309 ሲቪል ሰዎች ለቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ተዳርገዋል።” ብለዋል።

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት /ተመድ/ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት (UNOHCHR) ጋር በጣምራ ካደረጉትና በትግራይ ክልል ላይ ካተኮረው ሪፖርት ቀጣይ የሆነ ሪፖርት መሆኑን ገልጾ በዚህኛው ላይ ግን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳልተሳተፈ አስታውቀዋል። ትግራይ ክልልም ሆነ ህወሓት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ላይ እምነት እንደሌለው ከዚህ ቀደም ማስታወቁ ይታወሳል።

በተጨማሪም በጦርነቱ ወቅት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዳፈፀመ በተደጋጋሚ መግለፁ አይዘነጋም።

XS
SM
MD
LG