የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ትናንት ማምሻው የሩሲያ ዩክሬንን ግጭት እንዲያሸማግሉ ተጠይቄያለሁ ያሉ ሲሆን ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ መነጋገራቸውን እና ሁኔታዎቹ በድርድር ሊፈቱ እንደሚገባ ለፑቲን አስታውቂያለሁ ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳንቱ “ከሩሲያ ፌዴሬሽን ጋር ብሪክስ በተሰኘው የብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የገበያ አጋርነት በኩል ባለን ሥምምነት የተነሳ ደቡብ አፍሪካ የአደራዳሪነት ሚና ሊኖራት ችሏል” ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ራማፎሳ ለአደራዳሪነት ማን እንደጋበዛቸውም ሆነ ከሁለቱ ሃገራት ጋር በምን ዓይነት መልኩ እንደሚሰሩ ዝርዝሩን አልተናገሩም፡፡