በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉቴሬዥ የሶሪያን ጦርነት ለማብቃት ቁርጠኛ እንሁን ሲሉ ጥሪ አቀረቡ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ አስራ አንደኛ ዓመቱን የያዘውን የሶሪያ ጦርነት አስቁሞ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆን ያሻል አሉ፡፡

አንቶኒዮ ጉቴሬዥ “ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕጎች መከበር አለባቸው፤ ግጭቱ መቆም አለበት የሶሪያን ሕዝብ ልንተወው አንችልም” ሲሉ በመግለጫው ላይ አስታውቀዋል፡፡

ዋና ጸሃፊው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባመቻቸው የፖለቲካ ሂደት ውስጥ በሶሪያ ጦርነት ተካፋይ የሆኑ ሁሉም አካላት “ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲያደርጉ” ሲሉ ጥሪ ያደረጉ ሲሆን አያይዘውም “ሰላምን መመረጥ አለብን” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG