የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባካሄዱት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ ኢትዮጵያ የወሰደችው አቋም ለዓለምም የሚጠቅም መሆኑን ገልፀዋል።
ጦርነቱ ቆሞ ሰላም እንዲመጣ የኢትዮጵያ ፍላጎት መሆኑን ተናገሩ። ከአንድ መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከሳውዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።
የአፍሪካ የዕድገትና ዕድል ድንጋጌ በምኅጻረ ቃሉ (አጎዋ) እንዲቋረጥ መወሰኑ እና ኤች አር 6600 የተሰኘውን ሕግ ለማፅደቅ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የሚደረገው እንቅስቃሴ ለረጅም ግዜ የቆየውን የሁለቱን ሃገራት መልካም ግንኙነት የማይመጥን መሆኑን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።