በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁከትና በደሎች እንዲቆሙ ባሸሌት ጠየቁ


ሁከትና በደሎች እንዲቆሙ ባሸሌት ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:40 0:00

ሁከትና በደሎች እንዲቆሙ ባሸሌት ጠየቁ

የተባበሩትን መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሸሌት ለሰሜን ኢትዮጵያ ቀውሶች መቀጠል “ምክንያት እየሆኑ ናቸው” ያሏቸው ሁከትና የበደል አድራጎቶች እንዲቆሙ ለኢትዮጵያ መንግሥት፣ ለትግራይ ኃይሎችና ሌሎችም የታጠቁ ኃይሎች” ጥሪ አስተላልፈዋል።

ጦርነቱ በመንግሥቱና በህወሓት መካከል ተቀስቅሶ ለ16 ወራት መዝለቁንና ከትግራይ ወደ አጎራባች ክልሎች መዛመቱን ያስታወሱት ባሸሌት ትናንት፣ ማክሰኞ ጄኔቫ ላይ በሰጡት መግለጫ ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶችና የሰብዓዊ ሁኔታዎች መበላሸት በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል።

ሁኔታው በመላ አካባቢው በሲቪሎች ላይ እየደረሰ ያለውን የሞት ጉዳትና የሲቪል ተቋማት ውድመት እንዳበዛውም የመብቶች ድርጅቱ ከፍተኛ ኮሚሽነር አመልክተዋል።

በዚህ ጦርነት ውስጥ “የማንም እጆች ንፁህ አይደሉም” ብለዋል ኮሚሽነር ባሸሌት።

XS
SM
MD
LG